banner

በሀገራችን የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ ተከፈተ

#FastMereja
የተለያዩ የህትመትና የማስታወቂያ ስራዎችን በመስራት የሚታወቀው ብላክ ዳይመንድ አድቨርታይዚንግ «ብላክ ዳይመንድ አፍሪካ የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ» በሚል የህትመትና የማስታወቂያ ትምህርትና ዕዉቀት ብቃትና ልምድ ባላቸው መምህራኖች በዘመኑ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ለማስተማር መዘጋጀቱን ተቋሙ በዛሬው እለት መስከረም 21/2017 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣው መግለጫ አሳውቋል።

ከአንድ ወር እሰከ ሶስት ወር ድረስ ለሚቆይ ጊዜ የባነር፣ የስቲከር ህትመት ማሽነሪ፣ ሲ ኤን ሲ ማሽነሪ፣ የሌዘር መቁረጫ ማሽነሪ፣ የህትመትና ግራፊክስ ዲዛይን፣ ላይት ቦክስ ማስታወቂያ፣ ኒዮን ላይት ማስታወቂያ፣ የማስታወቂያ ገጠማ፣ የማስተወቂያ ፕሮዳክሽን፣ እስቲከርና ባነሮች መለጠፍ፣ የኢንዶርና አውትዶር ማስታወቂያ ስራ፣ የማይካ ሪሊፍ ሙያ ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጿል።

ከነገ ጀምሮ 22 በሚገኘው ማሰልጠኛ ተቋሙ ለአንድ ሳምንት ምዝገባ እንደሚጀምር የብላክ ዳይመንድ አፍሪካ የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ መስራች አቶ ተስፋዬ ነጋሽ ገልጸዋል።

📷 FastMereja / ጥላሁን ደሳለኝ





Leave a Comment