0
አርሰናል ከፒኤስዤ ጋር ባደረገው ጨዋታ 76ተኛው ደቂቃ ላይ ሪካርዶ ካላፊዮሪ ከፋቢያ ሩዊዝ ጋር በነበረው ንትርክ የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ::
በዚህ መሀል ዴክላን ራይስ ለጣልያናዊው vape(ኤሌክትሮኒክ- ሲጋራ) የመሰለ ነገር ይሰጠዋል:: ጣልያናዊውም ተቀብሎ ከአፉ ጋር ያገናኘው እና ሲወረውረው ይታያል::
ነገሩ ግን vape(ኤሌክትሮኒክ- ሲጋራ) ሳይሆን ኤሌክትሮላይት ጄል (ላብ መተኪያ) ነበር:: ይህ ጄል በፍጥነት ሀይል እና ጉልበት ይሰጣል እናም ለሰውነት ቅልጥፍና ስለሚረዳ አትሌቶች ይጠቀሙታል::
ኤሌክትሮላይት ጄል በመሰረቱ እንደታሸገ ዓይነት ሀይል ሰጪ መጠጥ ነው:: ልክ ሪካርዶ ካላፊዮሪ እንዳደረገው አንዴ ወይም ሁለቴ መምጠጥ/መሳብ ነው:: እናም በጨዋታ ወቅት ተጫዋቾች ሜዳ ላይ አይጠቀሙት የሚል ህግ የለም::
አርሰናል 2-0 ፒኤስዤ
[ ሰላም ጎሳዬ በፋስት መረጃ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ]


7 comments
Selam doesn’t want selam! How do u think he uses cigarettes in front of Million fans and sport family?
😁👈
በጣም ጨንቆን ነበር!😕
ምንድነው በጠዋት ምታወዛግቡን
i see ማመን የተሳነው ህዝብ
እንደ ሲቲ ብዙ ክስ እንጠብቃለን
ጡዞ እየተጫወተ መስሎኝ ነበር🙄