banner

“ምናለ ጎበዝ ተማሪ ባልነበርኩ” እላለሁ

“ከሰው አልጨመርም። አብዝቼ እተክዛለሁ። ፊደል ያልቆጠረ ብዙ የማውቀው ሰው ቤት ንብረት አለው። የተሻለ ሕይወት ይመራል። እኔ ለምን ተማርኩ እላለሁ – አንዳንዴ። እንደሱ አይባልም – አውቃለሁ። ግን ምን ላድርግ? ወደ አእምሮዬ የሚመጣውን ነው የምነግርህ።

ውስጤ ጠንካራ ሆኖ ነው ከራሴ ያለሁት እንጂ ጭንቅላቴ እኮ ልክ አይደለም።

እንደ ባይተዋር ነው የምኖረው።

አንዳንዴ ለብቻዬ እያወራሁ ራሴን አገኘዋለሁ።

ጓደኛ የለኝ፣ ምን የለኝ። ሰው ሆነህ ከሰው ጋ መጨመር ካልቻልክ ማበድ ማለት አይደለም?

ከወር-ወር ኪሴ ባዶ ነው።ከቤት የማልወጣውም ለዚያ ነው። ታክሲ ውስጥ ሰው ባገኝስ ብዬ እሳቀቃለሁ። ከዚህ ሁሉ ለምን ቤት አልቀመጥም ብዬ ነው ያለሁ።

በቀደም ትዝ ሲለኝ ለባለቤቴ የተጋባን ቀን ከገዛሁላት ስጦታ ውጭ ገዝቼላት አላውቅም።

ባትነግረኝም ሞራሏ መጎዳቱ አይቀርም። ለልጄም እንደዚያው። ከዚህ በላይ ምን የሚያሳዝን ነገር አለ?

እኔ መምህር በመሆኔ እና እነሱ የመምህር ቤተሰብ በመሆናቸወ ተጎድተዋል። ምንም ጥያቄ የለውም። አንዳንዴ ‘ምናለ ድሮ ጎበዝ ተማሪ ባልነበርኩ’ የምለውም ለዚያ ነው።

ዘገባው የBBC አማርኛ ነው።

10 comments

Tariku Mesfin October 2, 2024 - 7:23 am

What about am lazy that I expect my government to take of me and my family

Reply
Mesfin Mengesha Tosa October 2, 2024 - 7:28 am

የሀገሪቷ አሳፋሪ አሳዛኝ ታሪክ!!😭

Reply
Ashenafi M Hailekiros October 2, 2024 - 7:29 am

እኔ ህፃን እያለሁ የተማረ ሰው ኣሪፍ ኑሮ ነበረው እኔም ኣሪፍ ኑሮ እንዲኖረኝ በቀን የ 5 ስዓት የእግር መንገድ ለ 8 ዓመታት ተመላልሼ Elementary ጨርሼ high school and preparatory ኣልፌ ዩኒቨርሲቲ ጨርሼ ሰቅዬ በዩኒቨርሲቲው ቀረሁ የማስተርስ እድሉ ተሰጠኝ እሱም ጨረስኩ ኣሁን ኣይደለም ለትዳር ለኣዳርም ኣልበቃ ብላኝ ይሄው ባለሁበት ቁሜ ልቀር ነው 🤣🤣🤣🤣 አረ ጌታ ያለህ ምነው 8ኛ ክፍል ላይ በወደቅኩ እያልኩ እገኛለሁ!

Reply
Kalkidan Dawit October 2, 2024 - 7:30 am

አካውንቱ ካላችሁ ወይም በአካል ማግኘት የሚቻል ከሆነ 🙏🙏🙏

Reply
Yirga Meku Aschenk October 2, 2024 - 7:32 am

ሰው ሲማር ከሚያገኛቸው ጥቅሞች ዋነኛው የእውቀት ነጣነት ነው! እሱን ካረጋገጥክ ፊደል ያለቆጠሩ ሰዎች ቱጃር ሲሆኑ እኛ ጦም ምናድርበት ምክንያት ግልጥ አልሆንልኝ ቢል! ብዙ አሰላስያለሁ! መደበኛ ባልሆነ መንገድ ጥናት አድርጌያለሁ! ከኛም ላይ ድክመት ይታየኛል! አብዛኞቻችን ተጓዳኝ ስራ የመስራት የስራና ንብረት ማፍራት ሀሳቡም ተነሳሽነቱም ብዙም የለነም! ።

Reply
Shimelis Agito October 2, 2024 - 7:32 am

The strength of a country lies in the hands of its educators. A government that overlooks its teachers sows the seeds of its own weakness.

Reply
Habtamu Sime October 2, 2024 - 7:37 am

17+ ዓመት ከእድሜያችንላይ አቃጥለን ምንም የለን

ፊደል ለምኔ ብለው የኮበለሉቱ ሚሊየነር አልፎም ተርፎ ቢሊየነር ናቸው 😏😏😏😏

ለምን ተማርኩ ብዬ እያማረርኩ ነው ያንሁሉ አመት ሌላ ነገር ተፍ ተፍ ብል ስንት ነገር ይኖረኝ ነበር 🥹🥹🥹🥹

Reply
Temesgen Workie October 2, 2024 - 7:41 am

አዎ! ጎበዝ ተማሪ ባልነበርን!!! በመከራ ሥራ ፈልገን ስናገኝ ክፍያው ለምንም የማይሆን ብቻ ከባድ ነዉ •••• ምንም ማለት አልችልም ••••

Reply
Ãlêñã Ayzãkson Ãå October 2, 2024 - 7:48 am

ለምን ተማርኩ የሁላችን ጥያቄ ነው የወደቂ ያቋረጥጡት የተሰደዱ ያሉበት ደረጃ ስናይ🤔?

Reply
ሶፊ መስፍን October 2, 2024 - 8:00 am

መማር ከችግር ጋር አይያያዝም ባለመማር እውቀት ማጣት እንጂ ማህበራዊ ቀውስን በእውቀት በኩል ማያያዝ አይቻልም የተማርነው ማወቅ ስላለብን እንጂ የተቸገርነው ደሞ በስራችን በምናገኘው ገቢ አልያም ስራ ባለማግኘት ነው እና ሁለቱም በየበኩላቸው አስተዋፅኦ አላቸው አንገትን ከሚያስደፋን ይልቅ አንገታችንን ደፍተን ብንሰራ ከዚህ በላይ ምን አለ የሀገሪቷ ኢኮኖሚ አልተቻለም😢

Reply

Leave a Comment