ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ፤ ከትላንት በስቲያ በተካሄደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ መጽደቁን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ። የደመወዝ ጭማሪው 92 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መጠየቁንም የገንዘብ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት፤ ከሁለት ወራት በፊት መተግበር የጀመረውን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት ለመንግስት ቅርበት ላለው ፋና ቴሌቪዥን በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው። አቶ አህመድ በዚሁ ገለጻቸው፤ የፖሊሲ ማሻሻያው “በጎላ መልኩ ማህበራዊ ጫና እንዳያስከትል” በወጣው እቅድ መሰረት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
ፌደራል መንግስት “በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለውን ማህበረሰብ የመደገፉ ወይም የመደጎሙን ስራ አጠናክሮ መቀጠል አለበት” የሚለው ከእቅዱ መካከል አንዱ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያው ይፋ በተደረገበት ወቅት፤ ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች “አስፈላጊ የደመወዝ ድጎማ እና ማሻሻያዎች” “ለተወሰኑ ጊዜያት” እንደሚደረግ መገለጹ ይታወሳል።
ይህ የደመወዝ ጭማሪ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ መስከረም 21፤ 2017 ዓ.ም በተካሄደው “የካቢኔ” ስብሰባ ላይ መጽደቁን አቶ አህመድ ተናግረዋል። ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ፤ “ለኑሮ ድጎማ ጭምር እንዲሆን” በማሰብ የተተገበረ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።
Via: Ethiopian Insider

10 comments
ይሔ ፊት ይመራሀል ቻለው
እሳት ላይ ቤንዚን!
ተወያየን አፀደቅን ስንቴ ነው የሚፀድቀው ? ስንት ጨመረልን ስራ ግብሩስ ተወያያቹበት ወይ ? ማንም ሰርቫንት አይሰማቹም ኑሮ ውድነት አቃጥሎታል .
ፈጣሪ ሲባርከኝ ከ3ኛ ክፍል አቋረጥኩ 15 ዓመት ተምሬ ቢሆን ኖሮ የሻይ በዳቦም አትበቃ ነበር ደሞዜ 😭☝
እንዲህ እያላቹ ምንም ላትጨምሩ የኑሮ ውድነቱን አባብሱት፣ እናንተ የራሳቹ ምቾት እንጂ የህዝቡ ችግር አይታያቹም
Mircha bicha yidres eyetewashen aniqexilim
መንግስት በመንግስት ሰራተኛው ጦርነት አውጆዋል
እንኳን ደስ ያላችሁ ያለን!🙂↕️
ደማችን አልቋል፣ ወዝ ብቻ ነን
ስለዚህ፣ “ደመ-ወዝ” ከምትሉን
“ወዝ-ወዝ” ብትሉ ይሻላል።
ደሞ ለወር አበባ ወዝ ወዝ።
በVAT መልሶ ለመውሰድ የታቀደ ቁጥር ብቻ ነው እንጂ በዜጎች ላይ ከዜሮ ድምር አልፎ ውጤቱ ነጌቲቭ ነው ::