banner

ገራድ ሃንሳር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል እና በትምህርቱ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፆ መታሰቢያ ሊቀመጥላቸው

ገራድ ሃንሳር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል እና በትምህርቱ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፆ መታሰቢያ ሊቀመጥላቸው እንደሚገባ የሾኔ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ::

መስከረም 7/2017 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የሰላማዊ ፖለቲካ ትግል ቀንዲል እና የስነ ሕይወት ተመራማሪ ለነበሩት ለገራድ ሃንሳር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሾኔ ከተማ የልቅሶ ስነ-ስርዓት እና የመታሰቢያ ፕሮግራም እየተደረገ ይገኛል::

በሾኔ ከተማ ሁለገብ ስታዲዮም በተዘጋጀው ስነ-ስርዓት የገራድ ሃንሳር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ቤተሰቦች ፣ ወዳጅ ዘመዶች ፣ የክልል እና የዞን የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በዞኑ ሚገኙ መዋቅሮችና ከባደዋቾ ክላስተር የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በልቅሶ ስነ-ስረዓት ተገኝተዋል ::

የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት አንጋፋው ፖለቲከኛ እና ተመራማሪ ገራድ ሃንሳር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሕይወት ዘመናቸው ታሪክ የማይረሳው በኩራት የሚወሳ አሻራ ማኖራቸውን በስርአቱ የተገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ለሀዲያ ቴሌቪዥን የተናገሩ ሲሆን በሰላማዊ የፖለቲካ መድረክ እና በሳይንስ ምርምሩም ዘርፍ ያበረከቱት አስተዋፆ የጎላ በመሆኑ መታሰቢያ ሊቀመጥላቸው እንደ ሚገባ ተናግረዋል::

የገራድ ሃንሳር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት ተከትሎ የተዘጋጀው የሀዘን መግለጫ ስነ-ስረዓት በሾኔ ሁለገብ ስታዲዮም እየተደረገ ይገኛል::

ናሆም ዩሐንስ ከፋስት መረጃ ከሾኔ





Leave a Comment