0
በ2016 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ 500 እና ከዚያ በላይ የሆነ ውጤት ያስመዘገቡ 484 የአዲስ አበባ ተማሪዎች ተሸለሙ።
ከ1ኛ እስከ 3ኛ ከፍተኛ ዉጤት ባስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች በተለይም በሀገር አቀፍ ደረጃ
1ኛ ከፍተኛ ዉጤት – 575 ባስመዘገበችው ተማሪ ሲፈን ተክሉ፣
2ኛ ውጤት – 573 ባስመዘገቡት ተማሪ ማዕዶት እስክንድር እና ተማሪ ሶሊያና ሀብታሙ
3ኛ ውጤት – 570 ባስመዘገበችው ተማሪ ያስሚን ከድር
እጅግ የኮራን ሲሆን ከተበረከተላቸው እውቅና እና ሽልማት በተጨማሪ የውጭ ሀገር የትምህርት እድል(Scholarship) ሽልማት አበርክተንላቸዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጿል።




