#FastMereja
“የንባብ ባህል ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ኹነቶች እየተካሄደ ያለው የንባብ ሳምንት በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ከተማ ተካሄደ።
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የንባብ ሳምንት ከዲላ ከተማ በመቀጠል በትናንትናው እለት በይርጋጨፌ ከተማ ተካሂዷል።
የየይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታደለ ጥላሁን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ በከተማዋ የንባብ ባህል መቀዛቀዝ በተማሪዎች ውጤት ላይ ጫና ማድረሱን ጠቅሰዋል።
የአገርን ጸጋና ባህል ለትውልድ ለማስተላለፍ የንባብ ባህል ወሳኝ መሆኑን የጠቀሱት የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ አካሉ ናቸው የንባብ ባህል እንዲዳብር ዩኒቨርሲቲው በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቅሷል።
በኢትዮጵያ በስነ ምግባርና እውቀት የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ከግብ እንዲደርስ የንባብ ባህል ማዳበር ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አባተ ካሳው ተናግሯል በስነ ምግባርና እውቀት የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር የንባብ ባህልን ለማዳበር የሚያስችል ስራ ማከናወን ያስፈልጋል ብለዋል።
አገልግሎቱ የንባብ ባህል ለማዳበር የሚጠበቅበትን ድርሻ ለመወጣት ጥረት እያደረገ እንደምገኝ ጠቅሰው፤ አብያተ መጻሕፍትን በመያዝ በየዓመቱ በአስር ከተሞች መሰል መርሐ ግብር እያካሄደ መሆኑን አቶ አባተ ተናግረዋል።
በመርሃግብሩ ላይም ለይርጋጨፌ ከተማ 660 መጻሕፍት ድጋፍ የተደረገ፣ ዛጎል የመፅሐፍት ባንክ 250 መፅሐፍት ድጋፍ አድርጓል የከተማ መስተዳደሩም በተለያየ ወቅት ድጋፍ ላደረጉ ግለሰቦች እና ተቋማትን አመስግኗል።





1 comment
ፈጣኑ የመረጃ ምንጫችን እናመሰግናለን።