banner

በሀገራችን አነስተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል:: መሬት መንቀጥቀጥ አላህ ባሮቹን ከሚያስፈራራበት እና ከሚያስጠነቅቅበ

በሀገራችን አነስተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል:: መሬት መንቀጥቀጥ አላህ ባሮቹን ከሚያስፈራራበት እና ከሚያስጠነቅቅበት ክስተቶች መካከል አንዱ ነው::

በእኛ እግር ዘወትር የምትረገጠው መሬት በጌታዋ ትዕዛዝ ትንቀጠቀጣለች:: ህዝቦች በወንጀል ሲዘፈቁ፣ ሽርክ እና ጥፋት ሲንሰራፋ፣ በምድራችን ብክለት ሲስፋፋ ጌታችን አላህ ሰዎች ከጥፋታቸው ታርመው ወደሱ ይመለሱ ዘንድ ማስጠንቀቂያዎችን ይልካል:: ከነዚህ ማስጠንቀቂያዎች አንዱ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው::

ይህ ማስጠንቀቂያ ካለንበት የወንጀል አረንቋ በመውጣት ወደ አላህ እንድንመለስ የማንቂያ ደውል ነው::

በሀገራችን የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ በትንሹ ተከስቶ ያለፈ ቢሆንም ከበድ ያለ ሆኖ ቢከሰት ባለንበት የወንጀል አረንቋ እንደተዘፈቅን ወደ ጌታችን ፊት የምንቀርብበት ሁኔታ ይፈጠር ነበር::

ይህ ከመሆኑ በፊት አሁን ላይ እድል አግኝተናል:: ወደ አላህ እንመለስ:: ጌታችንን አብዝተን ምህረትን እንለምን:: አላህ እንዲታረቀን ፣በእዝነቱ እንዲያየን በዱኣ ልንበረታ ይገባል

አላህ ምህረቱን ይለግሰን!
ዑስታዝ አቡበከር አህመድ

10 comments

Mohe Muste October 7, 2024 - 2:55 pm

ኡስታዜ❤

Reply
Selam Nega Yared October 7, 2024 - 2:58 pm

እውነት ኖ

የዛፍ ና የወንዝ አምላክ በጌታ በየሱስ በሆነው የድንግል ማርያም ልጅ የተወጋ ይሁን

Reply
Kalkidan Dawit October 7, 2024 - 2:58 pm

ገና ዜናው ሳይደርቅ መስበኪያ አደረጉት

Reply
Suwali Bint Ahyan Suwali October 7, 2024 - 3:01 pm

Hak bilewal Ustazachin❤

Reply
Nuredin Musibay Edrise October 7, 2024 - 3:07 pm

ከወንጀል ነፃ የሆነ ሰው የላም ስለዝህ
ሁላችንም ብንጠናቀቅ የተሻለ ነው

Reply
Singitan Hailu October 7, 2024 - 3:12 pm

እውነት ነው

Reply
Ananiya Azariya October 7, 2024 - 3:12 pm

ትላንትና እንዴት ደስ እንዳለኝ ሀብታምና ድሃ የተማረና ያልተማረ ኦሮሞና አማራ ስልጤና ጉራጌ ወላይታና ሲዳማ ኑዌርና አኝዋክ ሱማሌና አፋር አንድ የሆኑበትና ፈጣሪያቸውን የለመኑበት ታሪካዊ ቀን ነው እናም ሰዎች በሰከንድ ለሚያልፍ ህይወት እንዲህ ባንባላ ጥሩ ነው ለማለት ያህል ነው

Reply
ሀበሻዊ October 7, 2024 - 3:15 pm

አለህ ሆይ ወንጃለችንን መራን አንታ ሁሉን ቸይ መሪና አዛኝ ጌታነህና

Reply
Enuka Kulche October 7, 2024 - 3:28 pm

ምህረተአብ በማንቂያ ደውል ዙሪያ ካንተ አፀፋዊ ምላሽ እንጠብቃለን ያው እዩ ጩፋም የሆነ ነገር አክልበትና ሞቅ ያለ አጀንዳ ብትሰጡኝ ሲል የኪቺንቺኒ ማህበረሰብ ድምፁን አሰምቷል💪 ድል ለጎጃም እንቅጥቅጥ

Reply
Meme Meme October 7, 2024 - 3:29 pm

ኡስታዜ

Reply

Leave a Comment