#FastMereja
አሜሪካን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በትምሀርቱ ዘርፍ የሚስተዋለውን የጥራት መጓደል በመፍታት አንድ እርማጅ ወደፊት ለመጓዝ ራእይ ሰንቆ የዛሬ 6 አመት የተመሰረተ ሲሆን አስካሁን በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ለአምስተኛ ጊዜ በቅድመ ምረቃ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ያስተማራቸውን ተማሪዎች ዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል የቴክኖሎጂ ማስተዋወቅ እና የምርቃት ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡
የአሜሪካን ቴከኖሎጂ ኮሌጅ በመላው አለም ዝነኛ ከሆነው የአሜሪካው መሓርሺ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ (Meharshi International University) ጋር በመተባበር በሃገራችን የመጀመሪያ የሆነውን የኦንላይን ቴክኖሎጂ ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ በእንደህ እያለ ለሀገራችን የትምህርት ዘርፍ ለየት ያለ የማስተማር ሂደትን ይዞ በመምጣት በአንድ ግዜ አንድ የትምህርተት አይነት ብቻ መስጠት ከ90% በላይ ተግባር እና ስራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ተማሪዎች ለመመረቂያ የሚሰሩት የቴክኖሎጂ ውጤት አዳዲስና ጠቃሚ ለሀገርም ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረከት መሆኑ፣ ከዚህም በተጨማሪ በጥራት የተማረ ውስን ተማሪ ማስመረቁ ልዩ ያደርገዋል። ኮሌጁ በአሁኑ ሰዓት በድህረ ምረቃ ማለትም በመደበኛው መረሃ ግብር በማስተር አፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በማስተር ኦፍ ኮምፒውተር ሳይንስ እና በመጀመሪያ ድግሪ ማለትም በባችለር የኮምፒውተር ሳይንስ እና በባችለር የቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ፕሮግራሞች በርካታ ተማሪያዎችን ተቀብሎ በማስተማረ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።





3 comments
Online ?
ምነ ባትሰክሱን።
ወረቀት ሽያጩ እየተፋፋመላችሁ ነው ግን?
👉ህዝቤ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ማስተርስ ዲግሪ ለመያዝ ከ3_5 አመት አፈር ከደቼ ይበላል። የግል ተቋማት ደግሞ በ1 አመት አልያም በ6 ወር ማስተርስ ዲግሪ አስመረቅን እያሉ ወረቀት እየሸጡ ናቸው 😃😃😃😃😀😀😀😃😃
This is my Ethiopia