banner

ሀይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎቹን በመቄዶንያ አስመረቀ

ሀይሌ ቤስት በኢትዮጵያ 2002 አ.ም በማስተር ሀይለየሱስ ፍሰሀ የተቋቋመ የቴኳንዶ ክለብ ሲሆን አሁን ላይ በአራት ቅርንጫፍ በሰሚት ፣ ጎሮ፣ የካ አባዱ እና ቦሌ አራብሳ በማስፋት እያሰለጠነ የሚገኝ ክለብ ነው አንድ መቶ ሀምሳ ተማሪዎቹን በመቄዶንያ አስመርቋል፡፡

ይህን ዝግጅት ሀይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ ከአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን በምርቃት ዝግጅቱ ላይም የአዲስ አበባ ወ/ቴኳንዶ/ ፅህፈት ቤት/ ሀላፊ አቶ ጥላሁን ፣ ግሎባል ማስተር አረፋይኒ፣ ማስተር ተገኜወርቅ ፣ ኪክ ቦክሲንግ ማስተር ዴቭ ዳን ፣ አይ ቲ ኤፍ ገነት፣ ኢትዮጲስ እና ሌሎችም በርካታ ታላላቅ የ ወርልድ ቴኳንዶ ማስተሮች እና የክብር እንግዶች በተገኙበት ምርቃቱ ተካሂዷል፡፡

ለክቡር ዶ/ር ቢንያም በለጠ ለኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ላበረከተው ትልቅ አስተዋፅኦ ከሀይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ የክብር ጥቁር ቀበቶ ከማስተር ሀይለየሱስ ፍሰሀ ተሰቶታል::

ይህ በጎ ስራ የተሳካ እንዲሆን ከተለያዩ አካላት የ 85 ሺ ብር ድጋፍ ፣ ከ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፓርት 35,000 ብር ገንዘብ ድጋፍ ፣ ሀይሌ ቤስት ከአንድ ሺ በላይ ለሆኑ አረጋውያንን ምገባ እንዲሁም ለሶስት መቶ ሰው የሚሆን ሶፍት፣ ሳሙና፣ዳይፐር ፣ 35,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ እና የአልባሳት ስጦታ ተሰጥቷል ፡፡





Leave a Comment