የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር በሚሰሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎች የተለያዩ ስታንዳርዶችን አስቀመጠ። ከተማ አሰተዳደሩ በኮሪደር ልማት ሥራ ከተማዋ የበለፅገች፣ ውብና ማራኪ ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሁም ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት በይበልጥ ተመራጭ ለማድረግ ስታንዳርዱን ጠብቆ ተግባራዊ እንዲሆን በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቋል።
በከተማው የሚሰሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ዋና ዋና ስታንዳርዶችን አስቀምጧል በዚህም መሠረት :-
1ኛ የህንጻ ከፍታዎች በዋና መንገዶች ላይ G+6 እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት
2ኛ የከተማ ህንፃ ቀለማት ምርጫ ነጭና ቢጫ ውህድ /white and grey mix/ አንድ ህንፃ መቀባት ያለበት ሶስት አይነት ቀለም ብቻ ነው
3ኛ በኮሪደር የሚለሙ ቋሚ አጥር ግንባታ 1.50 ሜትር ሲሆን በሚካሄዱ ግንባታዎች ጊዜያዊ አጥሮች ከሁለት ሜትር በላይ ከፍታ ያለዉ ሆኖ አረንጓዴ ቀለም በኤጋ ቆርቆሮ ማጠር
4ኛ ዝቅተኛ ህንፃዎች ከመንገድ መራቅ ያለባቸው ርቀት (set back) አደባባዮች ዙሪያ 6 ሜትር፣ ለሎች መንገዶችን ተከትሎ 4 ሜትር፣ ከግለሰቦች ወሰን በኩል መሰኮት ከሌለው 2 ሜትር፣ መስኮት ካለው 3 ሜትር ርቀት መኖር አለበት
5ኛ በቀንና በማታ ዕይታን የማይረብሽ ውብና ሳቢ መንገድ ዳር መብራት ቀለም የመብራት ቀለም ከ3000K Warm LED በከተማው በሁሉም ዋና መስመሮች በከተማ ውስጥ ያሉ ንግድና ግለሰብ ቤቶች፣ ድርጅቶችና መንግስታዊ እና ሌሎች ተቋማት የማውጣት ግዴታ እንዳለባቸው አብራርተዋል።
የከተማው መዋቅራዊ ፕላን በሚያዘው መሰረት በከተማ ደረጃ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶችን ወጥና ተመሳሳይ በማድረግ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት ተፈፃሚ እንዲሆን ከተማ አስተዳደሩ አሳስበዋል ሲል የዘገበው የአ/ምንጭ መ/ኮሚዩኒኬሽን ነው።
