0
በጣም እየዘነበ ነው: መሽቷል: ወደ 3 ሰአት ገደማ ከዋናው አስፋልት ተገንጥሎ የሚያስገባውን ኮብልስቶን ይዤ ወደ ቤት እየገባሁኝ ነው አንድ ሱፍ ዝንጥ ብሎ የለበሰ ሰውዬ በዝናብ ውስጥ በፍጥነት ይራመዳል: ዝናብ እየደበደበው ነው: መጀመርያ አለፍኩት ካለፍኩት በኃላ ቆም አልኩኝና ወደ ኃላ ተመልሼ ቆምኩኝ ከዚያም መስኮቱን ወረድ አድርጌ “ና ግባ: ልሸኝህ ጨለማ ነው” አልኩት ፍርሃት ይታይበታል “አይ ይቅርብኝ” አለኝ “ኧረ ና ግዴለህም: ዝናብ አይደብድብህ” አልኩት “አይ ግዴለም ይሁን” ብሎ መራመዱን ቀጠለ የእውነት አዘንኩኝ: though I understand his concern and fear 👇🏾 ክፉ ጊዜ: ክፉዎች የጫሩብን ፍርሃት አብሮ ከመሄድ እና ከመደጋገፍ ይልቅ ዝናብ እና ጨለማ የሚያስመርጥ ፍርሃት
Via: ዘመላዕክ እንድሪያስ
10 comments
እውነት ነው የተረገመ ሀገር እና ህዝብ።
በእግር ምሄደው እኔ ሳልሆን አልቀርም🙂
ባነነብሽ አደል!😁😄😄
እኔ ደግሞ ሰውዬውን አምኜ ልሸኝህ ብዬ አልጠራውም ነበር🤔 እጅግ ክፉ ጊዜ መጣብን😓ያ ሀሉ ደግነት, መተሳሰብ ታሪክ እየሆነ ይገኛል;ያሳዝናል😒
ጊዜ ምን አረገ ጊዜ ይመጣል ይሄዳል እኛ ሰው እምንባለው ሰዎች ወደ አውሬነት ስለተቀየርን ነው ክፉወች እራሳችን ን
ዘመን ቁጥር ነው የከፋው ትውልዱ ነው እግዚአብሔር ጥሩ ቀን ያምጣልን🙏🙏💚💛❤‼
ሀቅ 😟 እኔ ከኋላዬ ሰው ካለ ራሱ ሰላም አይሰማኝም እንኳን መኪና ውስጥ ልገባ 😥
ሰው እንዴት ይተማመን የምሰማው እና የሚያየው ሁሉ አስፈሪ ሆኖበት!
ማንም ሰው ቢሆን እሺ አይልም እንዴት ይመኑ ስራውስ ሚሰራው እንደዚ ተደረጎ አደል
እኔ ደሞ እንደተቸገረ ሰው ገብቶ እየሄደ ሰውየው ላይ ፓውል የሰራ መስሎኝ ነበር እስከ መጨረሻ ሳነብ የነበረው፣ እናም ምን ለማለት ነው ፦ ልሸኝክ ያለው ሰውዬ ምን ተማምነው ነው 🤔 ነገሩ ከባድ ነው ለሁለቱም አካላት፣ ፈጣሪ እርስበርስ እንድንተማመን ያርገን🙌