banner

ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለ2017 የትምህርት ዘመን ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።

#FastMereja
ጌጅ ሰርቪስ ትሬዲንግ ሐውስ ዛሬ በስሩ የሚተዳደሩ የትምህርት ተቋማት እና ሌሎች ተቋማቱን አስመልክቱ ለሚዲያ ተቋማት መግለጫ ሰጥቷል።

ጌጅ ሰርቪስ ትሬዲንግ ሐውስ በስሩ ከያዛቸው ተቋማት መካከል:- ጌጅ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ፣ ኩዊንስ ኮሌጅ፣ ሶፍትኔት የሥልጠና ማዕከል፣ ኤል ኤም ኢንተርናሽናል ሆቴል ስኩል፣ ግሬስ ኮሌጅ፣ ጌጅ አካዳሚ፣ MGK printing enterprise፣ AGET (African Global education & Technology )፣ AIHD (African international humanitarian development )፣ SMS trading plc ሲሆኑ በነዚህ ተቋማት ለበርካታ ዜጎች የትምህርት አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ ተገልጿል።

በ2017 የትምህርት ዘመን የክፍያ ቅናሽ መደረጉን የጌጅ ሰርቪስና ትሬዲንግ ሃውስ ፔኤልሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሞገስ ግርማ አስታውቋል በዚህ መሰረት:- ለቴክኒክ እና ሞያ ወራዊ ክፍያ 800 ብር የነበረው 600 ብር ሆኗል፣ ለመጀመሪያ ዲግሪ 900 ብር የነበረው 700 ብር፣ ለሁለተኛ ዲግሪ 1800 ብር የነበረው ወደ 1400 ብር መቀነሱን አቶ ሞገስ በመግለጫቸው አስታውቋል።

በተለያዩ ምክንያት መማር እየፈለጉ በአቅም ምክንያት መማር ያልቻሉ ዜጎች እስከ 50% ቅናሽ እና ሙሉ ስኮላርሺፕ በመስጠት በኮሌጃቸው እያስተማሩ እንደሆነ እና ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

📷 FastMereja





10 comments

Kalkidan Dawit October 14, 2024 - 6:02 pm

ለኬጂ 1ዲግሪ ስንት ብር ነዉ

Reply
Alemmeta Birhan October 14, 2024 - 6:02 pm

ኬጅ ነው ጌጂ

Reply
China Abdi October 14, 2024 - 6:03 pm

የወደቀ ቤት እንደዛ ነዉ!!

Reply
Mengistu Felege Guihon October 14, 2024 - 6:04 pm

ወረቀት ሻጮች

Reply
Miki Zerihun October 14, 2024 - 6:09 pm

ትውልዱ በአዲሱ የት/ት ፖሊሲ እና ዝቅተኛውን የሙሁራን የኑሮ ደረጃ እየተመለከተ በት/ት ተስፋ እየቆረጠ ኮሌጆችና ት/ት ቤቶች ባዶ እየሆኑ ስለመሆኑ ሁነኛ ማሳያ።

Reply
Melkamu Hailemariam October 14, 2024 - 6:13 pm

ትምህርት እንደማይጠቅምና ለትምህርት ሰው ገንዘብ ማውጣት እንደማያስፈልግ ስለገባው ነው። ነገር ግን ሁሉም መንግስትም ጭምር ተጨማሪ በምያስከፍልበት ወቅት መቀነሳችሁ ያስመሰግናል

Reply
Keros Gezahegn Keros October 14, 2024 - 6:13 pm

የእውነት ከሆነ ጥሩ ነው ሌሎቹስ?

Reply
Ezra Ayele Dushi October 14, 2024 - 6:13 pm

ዩንቨርስቲ College 😂😂😂

Reply
Tariku Tadesse October 14, 2024 - 6:17 pm

ከዚህ በኃላ ተከፍሎት እንኳን በተማረ::

Reply
Ephrem Tadesse October 14, 2024 - 6:19 pm

Great!!! especially for those people who want to upgrade their level of education.

Reply

Leave a Comment