#FastMereja l በየዓመቱ በሚካሄደው በ፵፫ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ዓመታዊ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ ከተሞችና ወረዳዎች የሚገኙ መንፈሳዊ የአብነት ትምህርት ቤቶች የመምህራንና የተማሪዎች መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት መቻሉ ተገልጿል፡፡
በአሰላ ማኅደረ ስብሐት በዓታ ለማርያም ቅ/ፋኑኤል ወቅ/ዮሐንስ ወ/ነጎድጓድ ገዳም በማኅበረ ቅዱሳን ከተገነባው ሕንጻ በተጨማሪ በመንፈሳዊ ትምህርት ቤቱ የመማርያ ክፍሎች አንዲሁም የመምህራንና የደቀ መዛሙርት ማረፊያ ቤቶች መሥራት ተችሏል ተብሏል፡፡
በሀገረ ስብከቱ በሽርካ ወረዳ ከ10 ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ 91 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ምእመናን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ሲል ሀገረ ስብከቱ በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም በደጁ ወረዳ ቡርቃ ጉራቻ ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚኖሩ 150 ምእመናን በጉሬ ደቢኖ ቅ/እግዚአብሔር አብና አርጆ ቅ/ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ምእመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን 499 አባወራና እማወራ ለስደት መዳረጋቸው ተነግሯል፡፡
ዘገባው የተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ነው

10 comments
ያኛው ብሄር ነው የሰዋቸው
እየሞቱ መመስከር ነው ተዋህዶነት
የተፃፈው ነው እየተፈፀመ ያለው!
የንጹሐን ደም ዋጋ ያስከፍላል!!!
ያማል ሞት የረከሰበት ምድር።
😭😭😭😭
ሁሉ የሚገፋህ ኦርቶዶክሳዊው ወገኔ 😭💔
በጣም ያሳዝናል መንግስት የሌለባት ሀገር 💔😭 መከራ ችግር ለኦርቶዶክስ አዲስ ነገር አይደለም ለሁሉም ግዜ አለው አሱ ይፈረዳል😭😭
በማን እንዴት
እራሱን ለመካላከል መሳሪያ ቢታጠቁ ኖሮ ስንት ያባሉ ነበር።