#FastMereja l በላይ አትክልትና አስቤዛ ማዕከል “የሚልየነሮች መንገድ” የተሰኘውን ፕሮጀክት በዛሬው እለት ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም በካሌብ ሆቴል በይፋ አስጀመረ።
በላይ አትክልትና አስቤዛ ማዕከል በሀገሪቱ እየታየ ያለዉን የሥራ አጥ ቁጥርን ከመቀነስ ባሻገር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ስለሚያደርገዉ የሚሊየነሮች መንገድ ፕሮጀክት ባስተዋወቁበት መድረክ ማዕከሉ ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት በርካታ አዋጭ የቢዝነስ ዘርፎች ላይ ጥናቱን ሲያካሄድ ቆይቶ በልምድ የተረጋገጠ የአስር ዓመት አዋጭ የቢዝነስ ዕቅድ በማዘጋጀት የዛሬ ሰባት ዓመት በ1500 ብር መነሻ ካፒታል አምስት ፕሮጀክቶችን ወደ ትግበራ በማስገባት ብቻ የጀመሩትን ቢዝነስ አሁን ባለበት ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አምስት መሸጫ ቦታዎች ትላልቅ የአትክልትና አስቤዛ ማዕከል ቅርንጫፎችን በመክፈት ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም ባሻገር በቋሚነት ከ75ሺ በላይ ደንበኞችን በማፍራት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ በመድረኩ ተነግሯል።
“በተባበረ ክንድ ድህነትን ታሪክ እናደርጋለን” በማለት ዉጤታማ ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ መሥራችና ባለቤት አቶ በላይ ሞርዴ ገልጿል።
ይህ ማዕከል ከዚህ ልምድ በመነሳት በቀጣይ ሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎችን በተግባርና በተጨባጭ ወደ ሚሊየነርነት የሚቀይር በልምድ የተረጋገጠ «የሚኒየነሮች መንገድ» የተሰኘ ፕሮጀክት በመንደፍ የቢዝነስ ፕላን በማዘጋጀት ለወጣቶች ፣ ለጀማሪ ነጋዴዎች እና በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተዉ ያሉ አምራችና አከፋፋዮች ሲጠቀሙበት የሥራ አጥ ቁጥርን በመቀነስ የስራ ባህላችንን ይበልጥ የሚያሳድግ ፕሮጀክት ላይ ኢንቨስት እያደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል።





10 comments
ሌላኛው ፐርፕዝ ብላክ ስምና መልክ ቀይሮ ካልሆነ መልካምነው ።
ቢሊየነር የነበሩትን ነው መቼስ
አሁን ሚሊየነር መሆኑ አደለም የከበደዉኮ ሚሊየን ብር ይዘህ በሬ እንጅ መኪና መግዛት አልተቻለም ነዉ መሰረታዊዉ ጥያቄ!
ተቨዱ🔥
Mud atezu genzeb yezu adersh yetno
ትልቅ ነበርን ትልቅም እኖናለን 😁😂😂 አይዞሽ ገለቴ😂😂
10 እማይሞላ ታዳሚ ይዞ ስለ ሚሊዬን ማውራት አይከብድም
ከእሱ በፊት እነሱ ቢሊየነር ሆነሉ🤔
በርቱልን ወገኖች
ቅድሚያ ለኔ።