banner

ኤልቬዜት ኢቨንትስ እንጦጦ ፓርክ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር አካሄደ

#FastMereja I ኤልቬዜት ኢቨንትስ ከአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እና ከአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች ጋር በመተባበር በጉለሌ ክ/ከተማ እንጦጦ ፓርክ ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር አካሂዷል።

“ውብ ከተማ ለመጭው ትውልድ!” በሚል መሪ-ቃል የፅዳት ንቅናቄው ተከናውኗል::

የኤልቬዜት ኢቨንትስ ዋና ስራ አስኪያጅ እንደገለፁት “ትውልድ የሚገለገልበትን ስፍራ በማፅዳት ጀምሮ በማፅዳት የመጨረስን ባህል እንዲያዳብር ያስፈልጋል ብለዋል” ከተማችን አዲስ አበባ ፅዱና ውብ ለማድረግ በተከናወነው ተግባር ቆሻሻ ሃብት መሆኑን ነዋሪው በመረዳት አወጋገዱም ሳይንሳዊ በሆነና አካባቢያዊ ተፅእኖ በማያሳድር መልኩ መሆን እንዳለበት ተገልጿል።

በንቅናቄ ስራው ላይም አመራሮችን ጨምሮ የፅዳት አምባሳደሮች የፕሮግራሙ አዘጋጆችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።





1 comment

አበበ ፍቅሩ October 20, 2024 - 11:55 am

ከነሱ መሀል እኮ ቂጡን ያልታጠበ ይኖራል

Reply

Leave a Comment