banner

ጎፈሬ ከኖቫ ኮኔክሽንስ ጋር ያለውን ስምምነት አደሰ

#FastMereja | ሀገር በቀሉ የስፖርት ትጥቅ ብራንድ ጎፈሬ ከአህጉራችን አፍሪካ አልፎ በሀገረ አሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ በሚከናወኑት ግራንድ አፍሪካ ረን እና ኢምፓክት አዋርድ ሁነቶች ብቸኛ የስፖርት ትጥቅ አጋር በመሆን ያለፉት ሁለት ዓመታት አብሮ የሰራ ሲሆን አሁንም ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የሁለቱም ሁነቶች አጋር በመሆን ለመዝለቅ ስምምነት ፈፅሟል።

ተቋማችንን ወክለው ወደ አሜሪካ ያመሩት ብራንድ አምባሳደራችን ኢንስትራክተር አብርሃም ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ አፍሪካውያን እና አሜሪካውያን አልፎም ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሰዎች በተሳተፉበት ግራንድ አፍሪካ ረን የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ላይ ከታደሙ በኋላ በማግስቱ ተወዳጇ ድምፃዊት አስቴር አወቀ እና ሌሎች ብርቅዬ የሀገራችን ሰዎች ዕውቅና በተሰጣቸው የኢምፓክት አዋርድ ሁነት ላይ የተገኙ ሲሆን ከዝግጅቶቹ አዘጋጆች ጋርም ስለ ጎፈሬ ሰፊ ውይይት አከናውነዋል። በሀገረ አሜሪካ እጅግ ተወዳጅነቱ እና ተቀባይነቱ እያደገ የመጣው ጎፈሬ የሁነቶቹ አጋር ሆኖ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት እንዲዘልቅም ስምምነት ላይ ፈፅመዋል።

በዚህም ጎፈሬ ከከፍተኛ የአጋር ተቋማት ዝርዝር ውስጥ በመግባት ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት አጋርነቱን ያጠናከረበትን ስምምነት የፈፀመ ሲሆን በሁነቶቹም ለዲያስፖራው ማኅበረሰብ አዳዲስ ነገሮችን ለማቅረብ በቅርቡ ቅድመ ዝግጅቶች እንደሚጀምሩ ይፋ ሆኗል።

ዓምና የዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ዘንድሮ ደግሞ በሜሪላንድ ግዛት የሞንቶጎሞሪ ካውንቲ አስተዳደር የጎፈሬን ምርቶች ጥራት በማድነቅ እንዲሁም የውድድሩ አጋር በመሆኑ የምስጋና ዕውቅና መስጠታቸው አይዘነጋም።

3 comments

ለገሰ ተፈራ October 20, 2024 - 6:58 pm

እንዴ…….ይሄ ነገር “ሾርኔ” ነዉ እንዴ??

ማነዉዉ ጐፈሬዉ 🙄

Reply
Endesh Girma October 20, 2024 - 6:59 pm

የሰላሌዋ ያምራል ጎፈሬዋ !

Reply
Hanny Konjo October 20, 2024 - 7:01 pm

ጎፈሬ ግን አይታየኝም ነው ዘፈኑን ነው
ጎፈሬ ጎፈሬ ጎፈሬ ሁኝልኝ ጎፈሬ ሁኝልኝ
እኔ አበጥራለሁ አንቺ ተዋቢልኝ 🤣🤣🤣

Reply

Leave a Comment