banner

በሐዋሳ ከተማ እየተገነቡ ያሉ ህንጻዎች ለከተማዋ ውበት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑ ተገለጸ።

#FastMereja I የሐዋሳ ከተማ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊና የኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዘርፍ ሀላፊ አቶ ተፈራ ቃጢሳ ከተማዋ በሀገራችን ካሉ ከተሞች ጽውብ ጽዱና ለኑሮ ምቹ መሆኗን አረጋግጠው ለዚህም በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ ህንጻዎች የበኩላቸው ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል።

አቶ ተፈራ አክለውም በከተማዋ የሚገነቡ ህንጻዎች የመንግስት ኘሮጀክቶችና የባለሀብቶች የዲዛይንና ቁጥጥር ስራው በህንጻ አዋጅና ደንቦች እየተመራ ይገኛል ብለዋል።

ከኘሮጀክቶች ቅድመ ጥናት ጀምሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ግምገማ በማድረግ ጭምር የሚሰራ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊው ዲዛይን ሲሰራ በህንጻ አዋጁ መሰረት ቢሆንም ወደ ትግበራ ሲገባ አንዳንዴ የሚገጥሙ ችግሮች እንዳሉ ጠቁመዋል።

በዚህም መነሻ ከተሰጠው ዲዛይን ውጪ የሚወጡትን በቁጥጥር ስራው እርምት እየተደረገ ስለመሆኑ አክለዋል።

በከተማዋ ሁሉንም ክ/ከተማ ባማከለ መልኩ የተጀመሩ ስራዎች፣ እየተገነቡ ያሉ ህንጻዎች፣ የኮሪደር ልማት፣ የሀይቅ ዳርቻና የታቦር ተራራ የልማት ስራዎች ሲጠናቀቁ ከተማዋ አሁን ካለችበት በተሻለ ሁኔታ ተቀባይነትና ምቹነት እንዲኖራት የሚያደርግና ተመራጭነቷን በብዙ ከፍ የሚደርግ ነው ብለዋል አቶ ተፈራ።

የከተማ ውበት የሚጠበቀው በመንግስትና ህዝብ ቅንጅት በመሆኑ ህንጻዎች በተቀመጠላቸው ዲዛይን ሊተገበሩ የሚገባ መሆኑን ሲጠቁሙ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓታችንና ንጽህና አጠባበቃችን በዚያው ልክ ሊሻሻል ይገባልም ብለዋል።

በዚህም አቶ ተፈራ አክለው በተደረጃ እና በተናበበ መልኩ የከተማችንን እድገት በቀኑ በፐርሰንት ለማሳደግ እንደ ከተማ በህብረት እየሰራን እንገኛለን ያሉ ሲሆን ህዝባችንን ከጎናችንን በመሆን እያገዘን ነው ብለዋል።





9 comments

Mahder Adane October 25, 2024 - 9:16 am

ደንቆሮ ውበት የሌለው G+2 ህንፃ ነውኮ የለጠፋችሁት

Reply
Tsegaab Dawit October 25, 2024 - 9:17 am

በሚገባ በከተማው የኮንስትራክሽ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አመርቂዎች ናቸው።

Reply
Jose Lemmish October 25, 2024 - 9:18 am

አብዛኛዉ ሀዋሳ ላይ የምገነቡ ህንፃዋች ከአራት ማዕዘን የዘለለ ድዛይን የላቸዉም።

Reply
Dagy Em October 25, 2024 - 9:20 am

አይ fastmereja ስታስቁ

Reply
Amare HF October 25, 2024 - 9:25 am

ህንፃዎቹን ቀጣይ Post ልታደርጉ መሆን አለበት🙃

Reply
Tile Enjose October 25, 2024 - 9:38 am

አንድም የሚያምር ህንጻ ከተማው ውስጥ የለም

Reply
Fekadu Hall October 25, 2024 - 9:42 am

ጥሩ ነው ነገር ግን ወደ አራቱም አቅጣጫ መስፋፋት አለበት በልማትም ሆነ በጥራትም በተለይ ሎቄ ቢለማ ሌላኛው ሀዋሳ እንደምፈጠር እርግጠኛ ነኝ

Reply
Simon B Barassa October 25, 2024 - 9:49 am

መናበብ ይቀራል አላሙራ ትምህርት ቤት ገቢ ማምጫ ተብሎ የተገነባው ለከተማው ውበት በግለሰብ ደረጃ እንዲ የሆነ መገንባት እንደማይችል ተነግሮ ለዚህ የተፈቀደው እንደገና ቢታሰብበት ጥሩ ነው

Reply
Yididya Yonas October 25, 2024 - 9:55 am

ምንድነው ይሄ ቀልድ ነው እንዴ የያዛቹት ሀዋሳ ፎቅ ብርቅ ነው እንዴ G+2 building የምታሳዪን

Reply

Leave a Comment