[ሰላም ጎሳዬ ለፋስት መረጃ]
ማርቲን ኦድጋርድ ለኖርዌይ በተሰለፈበት በኔሽንስ ሊግ ጨዋታ የቁርጭምጭሚት ጉዳት ማስተናገዱ ይታወሳል::
እንደ ብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ስቶል ሶርባኪን (Stale Solbakken) ከሆነ የአርሰናሉ አማካይ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ የሚመለሰውም በብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ነው በቀጣይ ወር::
ኖርዌይ ስሎቪኒያን ትገጥማለች ህዳር 12 ካዛክስታንን ከማስተናገዷ በፊት:: እናም ሶርባኪን”አሳማኝ ተስፋ” ሰጥተዋል የመድፈኞቹ አምበል በስብስባቸውም ለመካተት አካል ብቃት ላይ ያለውን ነገር እንደሚያረጋግጥ ተናግረዋል::
ኦድጋርድ መስከረም ወር መጀመሪያ ኖርዌይ ኦስትሪያን ባሸነፈችበት ጨዋታ ጉዳት ካስተናገደ በሗላ ለአርሰናል አልተጫወተም::
ሶርባኪን ለኖርዌው ጋዜጣ ቨርደንስ ጋንጌን (Verdens Gang) እንደተናገሩት “ሁሉም ነገር የሚያመላክተው (የኦድጋርድ ጉዳት) እንደታቀደው እና እንደታሰበው ነው እናም አሁን የመጨረሻው ደረጃ ላይ ነው መቼ ከቡድንህ ጋር ልምምድ ማድረግ አለብህ ከተጋጣሚህስ ጋር::
“የእርሱ ድርጊት እና ምላሽ ላይ የተመሰረተ ነው ነገር ግን ዝግጁ እንደሆነ እኛ አሳማኝ ተስፋ አለን::
“እኔ በደምብ አውርቼዋለሁ እድገት እና መሻሻል ማሳየት ጀምሯል ስለዚህ አሁን ጉዳዩ የልምምድ ነው(ልምምድ የማድረግ)::”
የአርሰናሉም አለቃ ሚኬል አርቴታ ባለፈው ቅዳሜ በቦርንመዝ ከገጠመው ሽንፈት በፊት በአስተያየቱ በቀጣይ ሳምንት እንደሚመለስ ተስፋ እንዳለው ተናግሮ ነበር::
ኦድጋርድ ማክሰኞ ዕለት የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በሜዳው ድል ባደረገው ቡድን አልተካተተም ነበር:: የለንደኑ ክለብ በፕሪምየር ሊግ እሁድ በኤምሬትስ ስታዲየም የሊጉን መሪ ሊቨርፑልን ያስተናግዳል::
