#FastMereja I በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ደመወዝ እንዲከፈላቸው ፊርማ በማሰባሰብ ላይ የነበሩ መምህራን ለእስር መዳረጋቸውን የታሳሪ ቤተሰቦች ገለፁ።
እስሩ የተፈጸመው መምህራኑ ከደመወዝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፊርማ በማሰባሰብ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አቤቱታቸውን ለማስገባት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት መሆኑን ዶቼ ቬለ ዘግቧል።
ፖሊስ መምህራኑ “አመፅ ለመቀስቀስ ተንቀሳቅሰዋል” እንዲሁም “የዞኑን ገጽታ አጥፍተዋል” በሚል ማሰሩን የታሳሪ ቤተሰቦች ገልፀዋል።
“ፖሊሶች ወደ ቤት ሲመጡ ምንም አይነት የፍርድ ቤት መያዣ ወረቀት አላሳዩም” ያሉት የመምህራኑ ቤተሰቦች አክለውም መምህራኑ ደሞዝ ይሰጠን ብለው የዳቦ ጥያቄ በማንሳታቸው ብቻ ታሰረውብናል ሲሉ ገልጸዋል።
እንዲሁም አንድ የዳሞት ወይዴ ወረዳ መምህር በበኩላቸው የፊርማ ማሰባሰብ ስራውን ሲያስተባብሩ ከነበሩት መካከል ሶስት በቅርብ የሚያውቋቸው መምህራን ለእስር መዳረጋቸውን ገልጸው፤ ከመታሰራቸው በፊት “እረፉ” የሚል ማስጠንቀቂያ ከወረዳው ባለሥልጣናት ተሰጥቷቸው እንደነበረ ገልጸዋል።
የዎላይታ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር ዎህዴግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ጎበዜ ጎኣ በበኩላቸው መምህራኑ ያነሱት የደመወዝ ጥያቄ ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው፤ “ደመወዝ የጠየቀን አመፅ ቀስቀሰሃል ብሎ ማሰር ከሥነምግባር ውጭ የሆነ ድርጊት ነው።” ሲሉ መግለጻቸውን ዶቼ ቬለ በዘገባው አመልክቷል።

10 comments
ለቤት ክራይ እና ለቀለብ ስላልበቃ አደል ደሞዛቸው ጭማሪ የጠየቁት😃
ይኸው ቤቱም ምግቡም ከመንግስት በነፃ👐
ይሄኔ የፈረሙት እኛንም በወሰዱን እያሉ ነው😉😄
ሰርቶ ከመብላት ታስሮ መብላ ሳይሻል አይቀርም 🤔
Nigusu Tesema
Jovani Gebeyehu
አያችሁ!?🙁🙁🙁
የምር የዚህ ሀገር መፍትሄው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ
ምንም አይነት መንግስት አያስፈልገንም….እኛው ህዝቦቿ እየተጨቃጨቅንም ቢሆን ብንኖር ከዚህ የተሻለ ነገር እናደርጋለን 😏
27 አመታት ጨለማ ነበር ?
አረ ወያኔ ማረን 🙏🙏🙏
በብልጽግና
ብዙ እናያለን ገና
ሳልፈልግ ነው የገጠመብኝ
ሳይሰሩ ሊበሉ ነዋ 😁
በዚህ ወቅት መብትህን የምታስከብረው በሀይል ብቻና ብቻ ነው።
እውነትም ብልፅግና ነው 👐👐