banner

እነርሱ እንዳሉት ነው… ደግሞም እውነት ነው። የእግርኳስ ክለብ ብቻ ነው ብሎ መግለፅ አይቻልም። ምክንያቱም እሱ ከክለብም በ

እነርሱ እንዳሉት ነው… ደግሞም እውነት ነው። የእግርኳስ ክለብ ብቻ ነው ብሎ መግለፅ አይቻልም። ምክንያቱም እሱ ከክለብም በላይ ነው…”Més que un club” ከክለብም በላይ ያሉት በብዙ ምክንያት ነው።

ስለ አረጎኔስ የነፃነት ዘመን የዘመሩት በርሱ ጥላ ስር ነው። ደቂቃ እየቆጠሩ 17 ደቂቃ ከ14 ሴኮንድ ሲሆን በሕብረት ቆሞ በ1714 በስፔን ንጉስ የመሰበርን ሕመም የገለጡት ለእርሱ ባነፁት ‘ቤተመቅደስ’ ውስጥ ነው። ጀነራል ፍራንሲስኮ ፍራንኮ ቋንቋቸውን እንዳይነገሩ አዋጅ ባስነገሩ ጊዜ በካታሉኛ መነጋገሪያ ብቸኛው ስፍራ ‘ቤተመቅደሱ’ ካምፕ ኑ ነበር። INDEPENCIA እያሉ ስለ ነፃነት እንዲዘምሩ ያስቻላቸውም እርሱ ነው። ባህላቸውን ከመጥፋት የታደገ፣ በወደቁ ጊዜ ተስፋቸው፣ ነገን አሻግሮ ማያ ብርሃናቸው፣ ተሰብሮ እንዳይቀሩ ጋሻ የሆናቸው፣ በአንድ ጥላ ስር [በአንድ መቅደስ] ያሰባሰባቸው፣ በውጣ ውረድ ያልወረደ፣ በመከራ ብዛት ያልከሰመ…የአሸነፊነታቸው ሰንደቅ ብለውግራና…ባርሴሎና!

ለእርሱ በእግር ኳስ ሜዳ አሸናፊነት ብቻ አይበቃም። አሸናፊነት ሙሉዕ የሚሆነው ከውበት ጋር ነው። የሱ ውበት ውስጥ ነፃነት ትገለጣለች። በዛች ነፃነት የካታሉኒያ ነፍስ ሀሴት ታደርጋለች። ዮሃን ክራይፍ የሚሉት የተቀባ ሆላንዳዊ ወደ ቤተመቅደሱ በተጠራ ጊዜ የዓለም እግርኳስ በጣሊያን ካቴና ተጠርንፎ በካቴናቾ ጭቆና ስር ይማቅቅ ነበር። ሰውየው ብዙ ደቀመዛሙርትን ከማፍራቱ በፊት ኳስን ከጭቆና አላቆ ነፃነትን በውበት ገለጠ። የበዛ ነፃነት፣ በሕብረት መስራት፣ ፈጠራ እና ክህሎት፣ ብዙ መቀባበል፣ ብዙ መተጋገዝ የአሸናፊነት ተምሳሌት…የካታሉኒያ ፓለቲካል ኢኮኖሚ በኳስ ሜዳ ነፃነት!

በዚህ መንገድ ኤስፓኞል የሚሉትን የውስጥ አቃጣሪ በየጊዜው እየደፈቀ…ከግዙፉ የካስቲያ ዙፋን..ከስፓኝ ነጩ ሮያሊቲ ምልክት ጋር ትከሻ እየተለካካ.. አሸናፊነት ላይ ውበትን ደርቦ ዛሬም ትልቁ የካታሉኛ የልብ ትርታ…ጋሻና መከታ ሆኖ ዘልቀዋል።

ሁዋን ላፖርታ (ፕሬዝዳንቱ) ተጠየቁ። ምንድነው ከክለብ በላይ ብሎ ማለት..? ሞገደኛው ሰውዬ ይመልሳሉ።

[እሱን ባይኖረን ኖሮ እኛም እንደ ካታሉኛዊ አንኖርም ነበር]

Via: ጥላዬ ያሚ

2 comments

Hunde Sololo Tsegaye October 26, 2024 - 5:30 pm

Telaye yeleyal eko🤔🙏🤞

Reply
Teshale Tilahun October 26, 2024 - 5:44 pm

ድል ለአለማችን ሃያሉ ቡድን ሪያል ማድሪድ

Reply

Leave a Comment