banner

የሙታንን ሰላም እና ክብር መንካት ወንጀል ነው

‼️

እኚህ ከታች የምታዪዋቸው ልጆች መካነ መቃብር ሂዶ በጥሩንባ ታጅቦ እየጨፈሩ ያሉበት ቪዲዮ እዚህ መንደር ሲንሸራሸር እና አንዳንድ ሰዎች ሕጉ ምን ይላል ብሎ ስሜን ሜንሽን ሲያደርጉ ተመለከትኩ።

የልጆቹ ድርጊት ከሞራል አንፃርም ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ሲሆን በወንጀል ሕጋችንም ጭምር በወንጀልነት የተደነገገ ድርጊት በመሆኑ ተጠያቂነት አለባቸው።

የወንጀል ሕጉ እንደሚከተለው ይደነግጋል👇
ማንም ሰው የሞተ ሰው ያረፈበትን ቦታ የደፈረ ፣ ያረከሰ የመቃብሩን ሀውልት ወይም ምልክት ያፈረሰ ወይም ያረከሰ ወይም የተቀበረውንም ሆነ ያልተቀበረውን አስክሬን ያረከሰ ወይም አካሉን የቆረጠ… በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ይቀጣል።

አበባየሁ ጌታ መምህር ጠበቃና የሕግ አማካሪ



Leave a Comment