የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ከተቀበሉት ከወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስቲያን በአሜሪካ (ELCA)፣ እና የስዊድን ቤተክርስቲያን (Church of Sweden) ጋር የጀመረችውን የግንኙነት ሂደት አስመልክቶ የቢፍቱ ቦሌ መካነ ኢየሱስ ማ/ም የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን በግልፅ ከተቀበሉ ከቀድሞ አጋሮቿ፣ የወንጌላዊት ሉተራዊት ቤተክርስቲያን በአሜሪካ (ELCA)፣ እና የስዊድን ቤተክርስቲያን (Church of Sweden) ጋር ማንኛውንም የመንፈሳዊ አገልግሎት እና የልማት ሥራ ግንኙነትን ማቋረጧ በ6ኛ፣ 7ኛ እና 8ኛ ካውንስል ላይ መወሰኑ ይታወሳል።
ነገር ግን በ8ኛው ጉባኤ የ“Rescue Mission” የመታደግ ተልዕኮ እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ከተወሰነበት ዓላማ ውጭ ውሳኔውን ሽፋን በማድረግ ከላይ ከተጠቀሱት አብያተ ክርስቲያናት ጋር የተለያዩ ግንኙነቶችን እያደረገች መሆኗ እየተስተዋለ ይገኛል ሲሉ በመግለጫቸው ገልጿል። በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ አድዋ ዜሮ ዜሮ ሙዚየም የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ባዘጋጀችው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ከላይ የተጠቀሱት አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች በክብር እንግድነት ተጋብዘዉ መገኘታቸዉ አንድ ማሳያ ነው ብለዋል።
ስለዚህ ይህ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን እና መሪዎች ዘንድ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል፡፡ በተጨማሪም በአማኞች መንፈሳዊ አገልግሎት እና አንድነት ላይ እንዲሁም በእምነታችን መስረት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድር እሙን ነው ሲሉ በመግለጫው ጠቅሷል።
የቢፍቱ ቦሌ መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን አመራሮች በጥቅምት 19 ቀን 2024 ልዩ ስብሰባ በማካሄድ እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ጥቅምት 20 ቀን 2024 ጉባኤውን በማሳወቅ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።
1. ከላይ ከተጠቀሱት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያለው ግንኙነት ከተቋረጠ በኋላ ከእነዚህ እግዚአብሔርን ቃል የሚፃረር ተግባር ጋር የሚተባበሩትን እና እግዚአብሔር ላይ ካመፁት ሰዎች ጋር የመታደግ ተልዕኮ (Rescue Mission) በሚል የሚደረገውን ማንኛውንም ህብረት የመፍጠር እንቅስቃሴ አጥብቀን እንቃወማለን!
2. ቀደም ሲል በ6ኛ፣ 7ኛ እና 8ኛ ካውንስሎች የተላለፉ ውሳኔዎች ያለ ምንም ትርጓሜ እንዲከበሩ!
3. የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ከፍተኛ አመራሮች ከወንጌላዊት ሉተራዊት ቤተክርስቲያን በአሜሪካ (ELCA)፣ እና የስዊድን ቤተክርስቲያን (Church of Sweden) ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ከማድረግ የማይቆጠቡ ከሆነ አመራራቸውንና የትኛውንም አገልግሎታቸዉን ፈጽሞ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
4. በአጠቃላይ ከግብረ ስዶማውያንን ጋር የትኛውንም ዓይነት ትሥሥርም ሆነ ግንኙነት ከሚያደርጉ ጋር ህብረት የማናደርግ እና የማንስራ ማሆነን አቋማችንን አፅንኦት እንገልፃለን፡፡
ሙሉ መግለጫውን በቴሌግራም ገፃችን ላይ ያገኙታል
📌 https://t.me/fastmereja
?? https://t.me/fastmereja

10 comments
Filimon Catho
Biyans lezbian yefkdlachew
ሲጀመር አንድ ናቸው ምንም ልዩነት የላቸውም
ነጮቹ እርዳታ ስላቆሙ ሲቸግራቸው ለክፉ አላማ ሊንበረከኩ ነው ማለት ነው። በየመንገዱ ዳር ሱቅ በደረቴ ቸርች እየከፈቱ ከሚጋፍፉት አትጠይቁም
😩😩😩😩😩😩😩😩😩😩🤣🤣🤣🤣
በድብቅ ግንኙት አላቸው እያላችሁን ነው እግዚኦኦኦኦ
ትክክለኛው ዉሳኔ ነዉ!👌
ምን ልዩነት አላቸውና😐
ምን አገባት በሌላው ሀይማኖት? ሲጀመር ተቋም አያስፈልግም ብለን ነው ከኦርቶዶክስ የወጣነው። ለተቋም ከተቋምማ ኦርቶዶክስ ምሉዕ ነበረች።
እየሱስን ብቻ ብለን እስከወጣን ድረስ ማንም ይሄን አምልኪ ያንን ተይ ሊለኝ አይገባም። እየሱስን የግል አዳኝ አድርጌ የተቀበልኩት ከተቋም ለመውጣት ነው።
እኔ በገባኝ መጠን ነው የማመልከው፣ ስለዚህ ማንም ከዚህ ወደዚህ የማለት መብት የለውም።
ሁላችንም ሉተራን ነን
በእየሱስ ስም Gay ወጋዉ