banner

ጎግል 17 የሩስያ መንግስት መገናኛ ብዙሀንን ከዩትዩብ ላይ ማገዱን ተከትሎ 20 ዴሲሊየን ዶላር ቅጣት እንዲከፍል ተወስኖበታል

የሩሲያ ፍርድ ቤት ጎግል ከዩቲዩብ ላይ የሩሲያ መንግስት የቴሌቪዝን ጣብያዎችን ማገዱን ተከትሎ 20 ዲሲሊየን ዶላር ($20,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000,000.) እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

ጎግል ምንም እንኳን ከአለማችን ትርፋማ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ቢሆንም የድርጅቱ አጠቃላይ ዋጋ ከ2 ትሪሊየን ዶላር የሚሻገር አይደለም፡፡

በዚህም የሩስያ ፍርድ ቤቶች የጣሉት ቅጣት 100 ተመሳሳይ ዋጋ ያላቸው ኩባንያዎች እንኳን ተደምረው ሊከፍሉት የሚችሉት አለመሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የተጠየቀው ገንዘብ ከአለም አቀፍ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት (ጂዲፒ) እድገትም የሚበልጥ ነው፡፡

እንደ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) መረጃ ከሆነ በአሁኑ ወቅት የአለም አቀፍ ጥቅል ሀገራዊ ምርት እድገት 110 ትሪሊየን ዶላር ነው፡፡

ቅጣቱ በ2020 ጎግል በሩሲያ አገልግሎት መስጠት ማቆሙን ተከትሎ ተጥሎ የነበረ ሲሆን በየቀኑ በእጥፍ እየጨመረ አሁን የሚገኝበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

በጎግል እና በሩስያ መካከል ቅራኔ የተፈጠረው የዩክሬን ጦርነት ከመጀመሩ ሁለት አመት ቀደም ብሎ የነበረ ሲሆን በ2022 የዩክሬን ጦርነት ሲጀመር ሌሎች ምዕራባውያን ኩባንያዎች በሞስኮ ላይ ተጽዕኖ ለማሳረፍ ግንኙነታቸውን ማቋረጣቸውን ተከትሎጎግልም ተመሳሳዩን አድርጓል፡፡

በዚህም ታዋቂዎቹን የሩስያ መገናኛ ብዙሀን አርቲ እና ስፑትኒክን ጨምሮ 17 መገናኛ ብዙሀን በዩትዩብ ላይ እንዳይገለገሉ ገጻቸውን አግዷል፡፡

እንደ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) መረጃ ከሆነ በአሁኑ ወቅት የአለም አቀፍ ጥቅል ሀገራዊ ምርት እድገት 110 ትሪሊየን ዶላር ነው፡፡

ቅጣቱ በ2020 ጎግል በሩሲያ አገልግሎት መስጠት ማቆሙን ተከትሎ ተጥሎ የነበረ ሲሆን በየቀኑ በእጥፍ እየጨመረ አሁን የሚገኝበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

በጎግል እና በሩስያ መካከል ቅራኔ የተፈጠረው የዩክሬን ጦርነት ከመጀመሩ ሁለት አመት ቀደም ብሎ የነበረ ሲሆን በ2022 የዩክሬን ጦርነት ሲጀመር ሌሎች ምዕራባውያን ኩባንያዎች በሞስኮ ላይ ተጽዕኖ ለማሳረፍ ግንኙነታቸውን ማቋረጣቸውን ተከትሎጎግልም ተመሳሳዩን አድርጓል፡፡

በዚህም ታዋቂዎቹን የሩስያ መገናኛ ብዙሀን አርቲ እና ስፑትኒክን ጨምሮ 17 መገናኛ ብዙሀን በዩትዩብ ላይ እንዳይገለገሉ ገጻቸውን አግዷል፡፡

በተመሳሳይ የሩስያ ሚድያዎች በአውሮፓ መስራት እንዳይችሉ ተከልክለዋል። ሞስኮም በተመሳሳዩ የምዕራባውያን ሚዲያዎች ከልክላለች፡፡

ይህ ሁኔታ በሞስኮ እና በግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መካከል ያለውን ቅራኔ እንዲባባስ እንዳደረገው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ቁጥሩን በትክክል እንኳን መጥራት እንደማይችሉ በይፋ ያመኑት የክሪምሊን ቃልአቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የጎግል አስተዳደር ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፡፡

ጎግል በሩስያ ፍርድ ቤቶች እንዲከፍል በተጠየቀው በምድር ላይ በሌለ ገንዘብ ዙርያ እስካሁን በይፋ የሰጠው መግለጫም ይሁን ምላሽ የለም፡፡

ከትሪሊየን በኋላ ያሉ ቁጥሮች እምብዛም ጥቅም ላይ ሲውሉ አይታዩም፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአንድ በአዋቂ እድሜ ላይ በሚገኝ የሰው ልጅ ሰውነት ውስጥ 7.1 ኦክታሊየን የአተም ቅንጣቶች እንደሚገኙ ሳይንስ ይናግራል፡፡

ዘገባው የዐል ዐይን ነው

10 comments

Elias Abebe Ab October 31, 2024 - 5:01 pm

በኢትዮጵያ ሰንት ይሁን 🙊🙉

Reply
Sewyalew Abel October 31, 2024 - 5:02 pm

ፅድቁ በቀረና አሉ።

Reply
Aynefam Alu October 31, 2024 - 5:06 pm

ይሄን ቁጥር ዛሬ በአርባ አመቴ አየሁ አይቼም አልገባኝም

Reply
መታገስ ዋጋ አለው October 31, 2024 - 5:08 pm

አለም ነው የተቀጣው።

Reply
Wonde Namja October 31, 2024 - 5:13 pm

ሩሲያ በጎግል ላይ የጣለችው ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ሞስኮ በድንበሯ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የውጭ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ እያሳየች ያለውን አቋም የሚያጎላ ነው። የሥነ ፈለክ ተመራማሪው በተለይ ዩቲዩብ ባሉ መድረኮች ላይ ብዙ የሚዲያ አውታሮችን በመከልከሉ ሩሲያ በምዕራቡ ዓለም ተጽዕኖ ላይ የምታደርገውን የመገፋፋት መጠን ያሳያል። ምንም እንኳን ቅጣቱ ተግባራዊ ባለመሆኑ ምሳሌያዊ ቢመስልም ሩሲያ በዲጂታል መድረኮች ላይ ሉዓላዊነትን ለማስፈን እና በድንበሯ ውስጥ ያለውን ትረካ ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጥረት ያሳያል። ይህ ርምጃ ሌሎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሩሲያን ህግጋት እንዳይቃወሙ ተስፋ ሊያስቆርጥ ይችላል፣ ይህም የአገሪቱን ዲጂታል ድንበሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የፖላራይዝድ መልክዓ ምድር ላይ በማጠናከር ነው።

Reply
Melkamfrie Jejaw October 31, 2024 - 5:13 pm

ወይ ጆሮዬ ስንቱን ቀጥር
አሰማኸኝ ጃል!ተመስገን ነው እሄንንስ ማን አየበት!

Reply
Esma Naik October 31, 2024 - 5:13 pm

ዲሲሊዬን ምን ለማለት ነው
ወሺንግታን ዲሲ ለማለት ፈልገቹ ነው አይደል

Reply
Sofi Bint Muhamd October 31, 2024 - 5:28 pm

እንደዚህም አይነት ቁጥር አለ😳😳🙆‍♀️🙆‍♀️

Reply
Beza Tesfay October 31, 2024 - 5:36 pm

አይ እሩሲያ ሁሌም እንዳስገረመችን 😄😄ምን ታርገው ጀግና መሪ ሰጣት

Reply
Yimelis Kassahun October 31, 2024 - 5:42 pm

አረ ሩስያ ቁጥር አይፈሩም

Reply

Leave a Comment