banner

ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ብሄራዊ ማህበር የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት በድምቀት ሊያከብር ነው፡፡

…
ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር በ1987 ዓ.ም የአእምሮ ዕድገት ዉስንነት ባለባቸዉ ወላጆች የተቋቋመ ሀገር በቀል ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ ዋና ዓላማው የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ዜጎች በሞያና ቴክኒክ ስልጠና መደገፍ፣ ተዛማጅ እገዛዎችን በማድረግ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ወገኖቻችንን እና ቤተሰቦቻቸውን ተጠቃሚ ማድረግ፣ስለ አእምሮ ዕድገት ውስንነት የሕብረተሰቡን ግንዛቤ መለወጥ፣ የአእምሮ ዕድገት ዉስንነት ላለባቸዉ ሕጻናት የአካቶ ትምህርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣ የአእምሮ ዕድገት ዉስንነት ባለባቸዉ ልጆቻቸው ምክንያት ለዝቅተኛ ኑሮ የተጋለጡ ወላጆችን በገቢ ማስገኛ ስራ በማሰማራት በኢኮኖሚ እራሳቸዉን እንዲችሉና የኑሮ ደረጃቸዉ እንዲሻሻል በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰራ ማህበር ነው፡፡

ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር ዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2017ዓ/ም በማዕከሉ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የማህበሩ ፕሬዚደንት ወ/ሮ ምህረት ንጉሴ እንደገለጹት ፤ የማህበራችንን የ 30ኛ አመት የምስረታ በዓል የምናከብረው በማህበራችን ታሪክ ውስጥ ሌላ አዲስ ምዕራፍ የሚከፈትበት ተስፋ ስላለው ነው፡፡

ለእኛ ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ የ30 ዓመታት የማህበራችንን ጉዞ ማክበር ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል ነው፣ ይህም ለአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ዜጎች ድጋፍ ለመስጠት፣ ለመብታቸው ለመሟገት እና አካታችነትን ለመፍጠር ምን ያህል እንደተጋን እንድናሰላስል ያስችለናል። በእነዚህ ሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ፣ በትምህርት፣ በጤና እና በማህበራዊ ጥበቃ እድሎችን ከማሳደግ፣ ዜጎችን በራስ በመደገፍ እና ድምፃቸው እንዲሰማ እስከማረጋገጥ ድረስ አስደናቂ እድገት አይተናል ብለዋል፡፡

የ30ኛ ዓመት የምስረታ ክበረ በዓሉ ለሁሉም ጎብኝዎች ክፍት በሆነው ከጥቅምት 25 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ/ም በኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ በሚዘጋጅ ኤግዚቢሽንና የመዝናኛ ፕሮግራም ተጀምሮ ህዳር 05 ቀን 2017ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ይጠናቀቃል፡፡

Leave a Comment