banner

ፌዴሬሽኑ አመታዊ ጠቅላላ ገባኤውን እና የአስተማሪዎች ዓመታዊ የክብረ-በዓል ቀን ጋዜጣዊ መግለጫ አካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን የ2016 በጀት ዓመት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመልካ ኢንተርናሽናል ሆቴል አካሄደ፡፡

ፌዴሬሽኑ የ2015 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤውን ፣ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ሪፖርት እና የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት በማካሄድ የተጓደሉ ሥራ አስፈጻሚ ሹመቶችን አጽድቋል

ባለፈው በጀት ዓመት የክለቦች ውድድር፥የኦፕን ቶርናመንት ፥የታዳጊዎች ውድድር ፥የክ/ከተሞች ውድድር ማካሄድ መቻሉ፣ የሙያ ማሻሻያ እና መደበኛ ስልጠና ፥የፀረ-አበረታች ቅመሞች ስልጠና፥የስፖርት አዋዠ እና የአመራር እና የባለሙያ ስልጠናዎች ሌሎች ስልጠናዎች መሰጠቱ አበረታች መሆኑን የገለጹት የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ዋሲሁን በ2017 በጀት ዓመትም የክለብ ቁጥሮችን ማሳደግ እና ጥራት ላይ ጭምር በመስራት፥ብቁ ስፓርተኞችን በብዛት በጥራት ለማፍራት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የፌዴሬሽኑ የፕሬዘዳንት ተወካይ አቶ ሳሙዔል ፋሲል እና ማስተር በፍቃዱ ታደሰ የም/ፕሬዘዳንት ተወካይ አያይዘውም የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክቶች በመደገፍ እና የፌድሬሽኑን አቅም ለማሳደግ በሚሰራው ስራ ስፖንሰር ማፈላለግ እና የሃብት ምንጮችን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው የስፖርት አደረጃጀቶችን በየጊዜው በመፈተሽ በጠንካራ አመራር የሚመራበትን ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው በትኩረት እንደሚሰራ አስገንዝበዋል

ተወዳጅ የሆነውን የወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ለማስምፋፋት ስፓርት አፍቃሪያን ከስራ አስፈጻሚው ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ ያቀረቡት አቶ ጥላሁን ፌዳሬሽኑ ልዩ ልዩ ውድድሮችን ጨምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን እንደሚያመቻች ገልጸዋል

የጉባኤው ተሳታፊዋች ፌዴሬሽኑን ለማሳደግ ክለቦችን ለመደገፍና ስፖርቱን በሁሉም ክፍለ ከተማ ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራውን ስራ እንደሚያግዙ አረጋግጠው ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ትኩረት ተደርጎ እንዲሰራ አመላክተዎል

ጠቅላላ ጉባኤው የፌዴሬሽኑን የተጓደሉ የስራ አስፈጻሚ ምርጫ ያካሄደ ሲሆን
አቶ ሚዴክሳ ከበደ በፕሬዘዳንትነት
ማስተር በፍቃዱ ታደሰ በም/ፕሬዘዳንትነት
እንዲሁም አርአያ ብርሃኔ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴነት ተመርጧል

2ኛ,በጠ/ጉባዔው በስፖርቱ ቤተሰብ ልዩ የሆነውና እነደሀገር አቀፍም የመጀመሪያ የሆነው የወርልድ ቴኳንዶ የአስተማሪዎች ዓመታዊ ክብረ-በዓል ቀን በጉባዔው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠበት ሲሆን በፕሮግራሙም ሲኒየር እና ጁኒየር አሰልጣኞች ባሉበት በየዓመቱ ታህሳስ 24 ቀን እንደአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ተግባራትና ዝግጅቶች ተከብሮ እንዲውል በሙሉ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን የዚህን ማስፈፀሚያ ፕሮግራምም ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር እርክክብ ተፈፅሟል።





Leave a Comment