banner

በካፋ ዞን የቡና ችግኝ ቆረጥክ በማለት የግድያ ወንጀል የፈፀሙ እናት እና ልጅ በእስራት ተቀጡ።

በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ፖሊስ መርማሪ ምክትል ሳጅን ዘካሪያስ ዘውዴ እንደገለፁት በወረዳው ጨራባ ቀበሌ ልዩ ስሙ አቢ ካካ ተብሎ በሚጠራበት መንደር ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ነው የግድያ ወንጀል የፈፀሙት፡፡ ተከሳሾቹ በቁጥር ሁለት ሲሆኑ ብዙነሽ አበበ እና አቤኔዘር ታከለ የተባሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አድርጎ በምርመራ እንዳረጋገጠው ሟች ለአንደኛ ተከሳሽ የቀድሞ ባለቤት እና ለሁለተኛ ተከሳሽ ደግሞ ወላጅ አባት ሲሆኑ ከሚስቱ ጋር በፍርድ ቤት ሀብት ንብረት ተከፋፍለው በፍቺ ተለያይተዉ መቆየታቸዉን ምክትል ሳጅን ዘካሪያስ ጠቁመዋል።

አንደኛ ተከሳሽ እና ሁለተኛ ተከሳሽ ወደ ማሳቸው ሲሄዱ ማሳ ላይ የነበረው የቡና ችግኝ ተቆርጦ በማግኘታቸው ችግኙን የቆረጠው ሟች ነዉ በማለት በእራሱ ማሳ ላይ እያለ ሁለተኛ ተከሳሽ ማለትም ልጅ በዱላ ማጅራቱን፣ ግራ እግሩን፣ ቀኝና ግራ እጁ ላይ እና የተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች ላይ ደጋግሞ አባቱን ይመታዋል፡፡

በመቀጠልም አንደኛ ተከሳሽ (ሚስት) በገጀራ ጭንቅላቱን፣ ቀኝ እጁ ላይ እና የተለያዩ የሰዉነት ክፍሎቹን ደጋግማ በመቁረጥ ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጋቸውን መርማሪው ተናግረዋል ።

ግለሰቦቹ በፈፀሙት ወንጀል የካፋ ዞን ዐቃቤ ህግ ግለሰቦቹን በፈፀሙት ከባድ የሰዉ ግድያ ወንጀል ክስ መስርቶባቸው የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀርባቸዋል።

የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዐቃቤ ህግ የቀረበለትን የክስ መዝገብ ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሾቹ የፈፀሙት ወንጀል በማስረጃ በማረጋገጥ የጥፋተኝነት ብይን ይሰጣል ፡፡

በዚሁ መሰረት የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቻለው የወንጀል ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ቡዙነሸ አበበ 2ኛ ተከሳሽ አቤኔዘር ታከለ እያንዳንዳቸው በ18 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላለፉን የደቡብ ምዕራብ ዚትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዘገቧል፡፡

4 comments

Efrem Tsehaye Mekonen November 1, 2024 - 9:36 am

ሟቹም ኮ ግድያ ፈፅምዋል ችግኙ ስለማይናገር ነው እንጂ

Reply
Negus Man November 1, 2024 - 9:36 am

እዉነትም ከፋ

Reply
Ge Gu November 1, 2024 - 9:38 am

ኧረ ጭካኔ

Reply
Tegegn Chinkisso November 1, 2024 - 9:38 am

እናት ባሏን ልጅ ደግሞ አባቱን😭😭😭እግዝአብሄርን ለማወቅ ባለወደዱት መጠን የማይገባዉን ነገር እንድያድርጉ ለማይረባ አዕምሮ አሳልፎ ሰጣቸዉ።

Reply

Leave a Comment