በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የዋጫሌ ወረዳ አሥተዳዳሪ የሆኑት ንጉሤ ኮሩን ጨምሮ ከ50 በላይ የሚሆኑ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ዛሬ ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም ማለዳ ላይ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው አማጺ ቡድን በተከፈተባቸው ጥቃት መገደላቸውን ዋዜማ ዘግባለች።
የወረዳው አሥተዳዳሪ፣ የዞን አመራሮች እንዲሁም በርካታ የመንግሥት ታጣቂዎች ታጣቂ ቡድኑ በስፋት ይንቀሳቀሳል ወደሚባልበት ካራ ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ ዛሬ ማለዳ 12 ላይ ለጸጥታ ስራ ተሰማርተው እንደነበር ዋዜማ ሰምታለች።
በስፍራው እንደደረሱም ታጣቂ ቡድኑ በከፈተባቸው ድንገተኛ ጥቃት የወረዳ አሥተዳዳሪውን ጨምሮ ከሃምሳ በላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወዲያው ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ የወረዳው የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊውን ጨምሮ በርካቶች ደግሞ ቆስለው ወደ ሙከጡሪ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የዐይን እማኞች ለዋዜማ አረጋግጠዋል።
በጥቃቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከሙከጡሪ ሆስፒታል ሪፈር ተጽፎላቸው ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን የገለጹት የዋዜማ ምንጮች፣ የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊያሻቅብ እንደሚችል ገልጸዋል።
ንጉሤ ኮሩ ከዚህ ቀደም በዞኑ የአለልቱ ወረዳ አሥተዳዳሪ በመሆን፣ በዞኑ ደግሞ በተለያዩ ኃላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፣ በቅርቡ ደግሞ የወጫሌ ወረዳ አሥተዳዳሪ ሆነው መሾማቸውን ዋዜማ ባደረገችው ማጣራት መረዳት ችላለች።
ዘገባው የዋዜማ ነው።

10 comments
እስከመች እርስ በእርስ መተላለቅ እግዞዮ
ተሞትን ተለማምድነው😪
መተላለቅ ብቻ። ከአአ ያለፈ ደህንነት ያለሰፈነ መንግስት።
ጉአደኛዬ ነብስህ በሰላም ትረፍ😔😔😔
Yihe new ሸኔ beka teketatele malet adl ahun ግባለት💪
በተመሳሳይ ሰአት ጠቅላይ ሚኒስተሩ በፓርላማ አባላት ፊት አንድ ከ 500 አመት በፊት የኖረ ነገር ግን ከመቃብር የተነሳ የፓርላማ ዉክልና የተሰጠዉ የአዳማ ከተማ ነዋሪ ሰዉ ጋር እያወሩ ነበር።
Betam yigeraml yhew hospital kuchibilenal wandimachin ayanu iju egru jerbaew temeto betam yasazinal.mengisti siraw mindew??
silaa maal goona #_”Nugee nagaan boqodhu!
ወይ ኢትዮጵያ 😥😥 በነፃነት መንቀሳቀስ ልናፍቀን ነው ከዚህ በኃላ በየ ሀይማኖታችን ፈጣሪን እንለምነው ወገኖቼ የለንበት ጊዜ ከፍቷል የምንሰማው ነገር ሁሉ የሚዘገንን ሀዘን ነው ያረቢ መረን 😥
እና ምን ይጠበስ