banner

የትግራይ ሰራዊት ታጋይ በወልዲያ ጎዳና ወደቀች ተብሎ የነበረው ሮማን ጉዑሽ ቅመም እርቅይሁን ሆና ተገኘች

#FastMereja I ነገሩ እንዲህ ነው… ወጣት ሮማን ጉዑሽ ከጥቅምት 9/2017 ዓ/ም ጀምሮ የትግራይ ሰራዊት ታጋይ ሆና በውግያ ቆስላ በወልድያ ከተማ ጎዳና ወድቃ እንደምትገኝ በተለያዩ የማህበራዊ ኣውታሮች ተሰራጭቶ ነበር ያለው የትግራይ ፖሊስ ሆኖም በወልድያ ከተማ ህዝብ፡ በሃገር መከላከያ ሰራዊት፡ በትግራይ ህዝብና መንግስት እንዲሁም በለጋሽ ባለሃብቶች ጥረት፡ ትብብር እና ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ከተማ እንድትመጣ ከተደረገ ቡኃላ ለኣጠቃላይ ህክምና መቐለ በሚገኘው ዓይደር ኮምፕርንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በልዩ ክፍል (Special Room) ልዩ የሀክምና ክትትል ከተደረገላት በኃላ ሁኔታዋ መሻሻል ኣሳይተዋል።

በመሆኑም ኣድራሻዋ በሚመለከት የትግራይ መንግስት ኣስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ ቡኃላ ስሟ ሮማን ጉኡሽ ሳይሆን ቅመም እርቅ ይሁን ደረበ የትውልድ ኣድራሻዋ ትግራይ ክልል ሳይሆን በኣማራ ክልል ሰ/ጎንደር ዞን በየዳ ወረዳ ማጥበ ሃረገወይን ቀበሌ እንደሆነችና የቅርብ የስጋ ዘመድዋ ዲያቆን ቢረሳው ኣገኘሁ ገበየሁ ፈርመው መረከባቸውን የትግራይ ፖሊስ ዘገባ ተመለክተናል።




Leave a Comment