0
ጥቅምት 17/2017 ዓ/ም ከቃፍቲያ ሁመራ ባዕከር ቀበሌ አንድ የ6 ዓመት ህጻን ልጅ ለማገት የሞከሩ ግለሰቦች በፖሊስ እጂ ከፍንጅ ተይዘዋል።
ከህጻኑ ወላጆች በቀን ሰራተኝነት ተቀጥረው ሲሰራ የነበረ አጥሩ ቆየ ውብሸት የተባለ ግለሰብ እና ግብረአበሩ ገጣለው /ኮኬ/ ምህረት አያሌው የተባሉ ግለሰቦች ህፃኑን ከቤቱ አታለው በማውጣትና በማገት ወደ ጎንደር ከተማ አምጥተው በማገት ለህጻኑ ወላጆች ስልክ በመደወል 700,00 (ሰባት መቶ ሺህ ብር) እንዲከፍሉ ይጠይቃሉ።
የኋላኋላም ጉዳዩ የደረሰው ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ክትትል በማድረግና የድርጊቱን ሁኔታ ያዩ ግለሰቦች በተሰጠ ጥቆማ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 16 ብላጅግ ቀበሌ የደን ጫካ ውስጥ ጥቅምት ቀን 21/2017 ዓ/ም ከቀኑ 10:00 ሠዓት አካባቢ በጎንደር ከተማ ፖሊስ እጅ ከፍንጅ በመያዝ አስፈላጊው ምርመራው እየተጣራ የሚገኝ ሲሆን ውሳኔውንም ፍርዱ እንደተከናወነ ውጤቱን የምናሳውቅ ይሆናል ሲል የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው የዘገበው።


2 comments
ሬሳም ማገት ጀመረ
Entrepreneur mehonachew nw a😂
Awey chigir