banner

#ልክ እንዳንተ ጌታችን ተገልጦ እንድናየው ንገርልን

ገና በ20 ዓመቱ በገዳመ አስቄጥስ የመነኮሰው ግብጻዊው መናኝ አባ ቢሾይ በ320 ዓ.ም ነበር የተወለደው፡፡ ለቤተሰቡ የመጨረሻና ሰባተኛ ልጅ ቢሆንም ልቡ ቅን እንደሆነ ያዬው እግዚአብሔር መርጦታል፡፡ መንፈሳዊ መጻሕፍት ማንበብ፣ መጾምና መጸለይ እጅግ የሚወዳቸው ነገሮች ነበሩ፡፡ በተለይ ለነቢዩ ቅዱስ ኤርምያስ ከነበረው ፍቅር የተነሳ ትንቢቱን ሲያነብ ምስጢሩ የቀረረበት ቦታ ላይ ነቢዩ እየተገለጠ ያብራራለት ነበር፡፡

ከትሕትናውና ከቅድስናው የተነሳም ጌታችን እየተገለጸ ያነጋግረው ነበር፡፡ ይህን የሚያውቁ የገዳመ አስቄጥስ መነኮሳት አባ ቢሾይን አንድ ልመና ለመኑት፡፡ “ልክ እንዳንተ ጌታችን ተገልጦ እንድናየው ንገርልን” አሉት፡፡ እርሱም ወደ ጌታችን ቢያመለክት በተራራው ራስ ላይ የምገለጥ ነኝና ሁሉም ወደዚያው እንዲወጡ ንገራቸው የሚል ምላሽ ከቀነ ቀጠሮ ጋር ሰጠው፡፡

በቀጠሮው ቀንም መናኞችና መነኮሳቱ ወደ ተራራው እየተሯሯጡ ይወጡ ጀመር፡፡ በመንገዳቸውም አንድ የደከሙ አዛውንት እኔም ጌታዬን ማየት እፈልጋለሁና ይዛችሁኝ ውጡ ብለው ቢጠይቁ ሁሉም ትተዋቸው ወጡ፡፡ በመጨረሻ የመጣው አባ ቢሾይ ግን ሽማግሌውን ገና ሲያያቸው አዘነላቸውና ሳይጠይቁት አባቴ ወደ ተራራው ራስ ተሸክሜ ልውሰዶት አላቸው፡፡ እርሳቸው ግን አይሆንም አሉት፡፡

ወደ ገዳማት ስንሔድ የሚኖረንን እሳቤ እዩት እስቲ፡፡ አንዳንዶቻችን ቅድስና ፈልገን ሔደን የምንይዛቸውን ቁሳቁሶች ብዛት ልክ የለውም፡፡ አባ ቢሾይ ምንም እንኳን ወደ ተራራው ራስ ለመሔድ ቢፈልግም የኖረበትን የቅን ልቡና ባለቤትነት ያለበትን ገዳማዊ ቦታ ቅድስና አልረሳውም፡፡ እናም አይሆንም ብሎ ተሸክሟቸው ተራራውም መውጣት ጀመረ፡፡

መጀመሪያ ላይ በጣም ቀለውት ነበር፤ እየቆየ ግን ክብደታቸውን መቋቋም ቢያቅተው ቀና ብሎ አያቸው፡፡ አስገራሚው ነገር ሽማግሌ መስሎ ከመንገድ የቆየው ጌታ ነበር፡፡ ሁሉም ወደ ተራራው ጌታን ሊያዩት በጥድፊያ ሲወጡ ጌታችን የሚወደውን ነገር ለማድረግ ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡ በኋላ አባ ቢሾይ ነገሩን ሲሰሙ አዘኑ፡፡

በረከት ለማግኘት ወደ ገዳማት ስንጓዝ የባህታውያኑን አኗኗር እያሰብን በአታቸውን የሚያጸና እገዛ ማድረግ አንርሳ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444

Leave a Comment