banner

ሞቢሊቲኢ ከድጋፍ ማይክሮፋይናንስ ጋር በመተባበር 17 ተሽከርካሪዎችን አስረከበ

#FastMereja I ሞቢሊቲ ኢ ከድጋፍ ማይክሮፋይናንስ ጋር በመተባበር ዛሬ ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም ለ17 የመኪና ፈላጊዎች የመጀመሪያ ዙር የBYD ሴጉል መኪኖችን አስረከበ።

ደንበኞች ዛሬ የተረከቡት የኤሌክትሪክ መኪናዎች በ14 በመቶ የቅድመ ክፍያ ብድር አገልግሎት እንደሆነ የሞቢሊቲ ኢ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሚኒሊክ ጌታቸው ተናግረዋል እያንዳንዳቸውም ከ2.8 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ መሆናቸው ተገልጿል።

የድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ስራ አስከያጅ አቶ ደረጀ በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር በአሁኑ ሰዓት አጫጭር ብድሮችን በመስጠት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

የBYD ተሽከርካሪዎች አስመጪ የሆነው ሞቢሊቲ ኢ በዓመት 1,000 የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ ለማስገባት በሞቢሊቲ ኢ፣ ፓክ ግሩፕ እና በሃንሰም ግሩፕ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ሁለተኛው ዙር የርክክብ ስነ-ስርዓትም በቀጣዮቹ 15 ቀናት ውስጥ እንደሚፈፀም ተገልጿል።

📷 FastMereja





1 comment

Tizazu Getahun November 2, 2024 - 6:42 pm

አበዳደሩንም አስረዱና

Reply

Leave a Comment