banner

አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን እና የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር ለመስራት ስምምነት አደረጉ።

#FastMereja I አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አክሲዮን ማህበር እና የኢፌዲሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችና ተቋማትን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ለወጣቶች ትምህርት እድልና ስራ ለማመቻቸት አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ሰነድ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም በኢፌዲሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንሰቲትዩት ዋና መስሪያ ቤት የፊርማ ስነ-ስርዓት አካሂደዋል።

አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ የማህበረሰቡን ችግር በቴክኖሎጂ ለመፍታት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለአገልግሎት እንዲውሉ እያደረገ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ከተለያዩ የመንግስትና የግል ዘርፎች ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ከሀገር ባለፈ በውጭ ሀገር የገበያ ዕድል ለመፍጠር ጭምር የሚያስችል የአሰራር ስርዓት በመፍጠር ከሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግስትና የግል ተቋማት ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አምራቾች ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸዉን ምርት ማምረት እንዲችሉ ቴክኒካዊ ድጋፍና የማሽነሪ አቅርቦት በማመቻቸት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የገበያ ዕድል፣ የክህሎት፣ የልምድ፤ አዳዲስ የፈጠራ ስራና የቴክኖሎጂ ልውውጥ የማመቻቸት ስራን በቅንጅትና በትብብር በመምራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።





Leave a Comment