0
አቶ አሰፋ ተዘራ ይባላሉ የሻኪሶ ነዋሪ ሲሆኑ በከተማው በልብስ ስፌት ስራ በመሰማራት በሚያገኛት ገቢ ቤተሰቦቻቸውን ያስተዳድራሉ ፡፡ ስራው አጥጋቢ ገቢ ባይኖረውም እግዚአብሔር ይመስገን ሳላማርር ባለኝ ነገር ደስተኛ ነበርኩ ነገር ግን ህይወቴን ለመለወጥ የማላደርገው ሙከራ አልነበረም ከሙከራዎቼ አንዱ ሎተሪን መቁረጥ ሲሆን ማን ያውቃል አንድቀን ይወጣ ይሆናል በሚል ተስፋ ትላልቅ ዕጣዎች ሲኖሩ ሙሉውን ቲኬት መቁረጥ አዘወትር ነበር በማለት አቶ አሰፋ ይናገራሉ፡፡
ታድያ እንደተለመደው ጳጉሜን 5 ቀን 2016 የሚጣውን የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ሙሉውን ቲኬት ይቆርጡና መውጫውን ቀን ይጠባበቃሉ ፡፡ ሎተሪው ከወጣ በ12ኛው ቀን ከሻኪሶ ወደ አዶላ በሄዱበት ድንገት የሎተሪ አዟሪ ሲያዩ የቆረጡትን የእንቁጣጣሽ ለለተሪ ትዝ ሲላቸው አሳዩትና እንዴ ጋሼ 5 ሚሊየን ብር እኮ አለው ሲላቸው የተደበላለቀ ስሜታ ተሰማኝ ይላሉ ፡፡
እራሴን አረጋግቼ ወደ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በመሄድ እውነትም የ5 ሚሊየን ዕድለኛ መሆኔን አረጋገጥኩ በማለት በደስታ ግልጸዋል ፡፡ ሽልማታቸውም በሚሩበት ቦታ ድረስ በመሄድ በህዝብ ፊት ተረክበዋል ፡፡

8 comments
እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ደስ አለህ
አይ ሎተሪ አዟሪ 😔
የ ጠፋው ወንድምህ ይፈልግሃል 🙄
እግዚአብሔር ይመሰገን ደሰ. ይላል
ልጁ ነኝ እንኳን ደስ አለን
Emebetetachin kezh sqay nuro awotachih…lebetekrstyan gin adera!!!
አሁን ገና #ገንዘብ ቦታዋን አገኝች እኮን ደስ አለህ🥰
ምንም የማይሳነው እግዚአብሔር የዕድል በሩን ሲከፍትልህ እንዲህ ነው ክብር ምስጋና ይግባህ🙏🙏🙏