banner

በአርቲስት ታማኝ በየነ የሚመራው ግሎባል አሊያንስ ለአፋር እና ለአማራ ልማት ማህበራት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ግሎባል አሊያንስ ለኢትዮጵያ መብት ለአማራ ልማት ማሕበርና ለአፋር ልማት ማሕበር ከዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መበቶች ጋር በመተባበር ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለማቋቋም ግንባታዎችን ለማካሄድ ይረዳ ዘንድ ለእያንዳንዳቸው የሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሀያ ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ዛሬ ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ቦሌ ማተሚያ አጠገብ በሚገኘው በአዲስ አበባ አልማ ጽ/ቤት አዳራሽ የገንዘብ
ርክክብ ሥነ ሥርዓ አካሂዷል።

በአርቲስት ታማኝ በየነ የሚመራው ግሎባል አሊያንስ ባለፉት ስድስት ዓመታት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን በእርዳታ የተገኘውን ይህን ገንዘብ በአፋር የሎጊያ ትምህርት ቤት ቤተ መፅሀፍት ሲገነባበት በአማራ ደግሞ በደቡብ ወሎ የሚገኘው ቢስቲማ ትምህርት ቤት ላይ አንድ ህንፃ ይገነባበታል ተብሏል።





1 comment

Tesfaye Moges November 6, 2024 - 9:04 am

ይሄ ሌባ ጫማ ለሺ ለአማራ ህዝብ በህይወት ዘመኑ አንድም ርዳታ አለማድረጉ ያሳዝናል

Reply

Leave a Comment