banner

ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አድነት ገዳም ይባላል።


በማዕከላዊ ጎንደር ምስራቅ በለሳ ወረዳ ይገኛል።
ይህ ገዳም ከዘጠና በላይ መነኮሳትና በመቶ የሚቆጠሩ ፀበልተኞች የሚገኙበት እጅግ ድንቅ ተአምር ያለበት ገዳም ነው።
በአለት መሀል የሚገኝ ማር በመነኮሳት ፀሎት ብቻ አየተቆረጠ ለፀበልተኞች የሚሰጥ ለምእመኑ እንደ እምነት ያገለግላል።
ፀበሉ እንደስሙ ሙት ያስነሳ ፣ ብዙ ድዉያንን የፈወሰ ፣ ህመምተኞችን ወደ ጤናቸው የመለሰ ነው።

በዚህ ድንቅ ተአምር ያለበትና ታሪካዊ የአንድነት ገዳም ውስጥ የሚኖሩ መነኮሳት ታዲያ ትልቅ አደጋ ተጋርጦባቸው ይገኛል።
በአንድ በኩል አከባቢው ተፈጥሮ ፊቷን አዙራበት በድርቅ ምክንያት ምንም ዓይነት አዝርእት አልበቀለበትም፣ ጭው ያለ ምድረ በዳ ሆናል።
ወዲህ ደግሞ ባለው ጦርነት ምክንያት በትልቅ ችግርና ፈተና ውስጥ ተከበው ይገኛሉ።
በየጊዜው ይጎበኟቸው የነበሩ ፀበልተኞችም በአሁኑ ሰአት በችግሩ ምክንያት ምንም ዝር ብለው አያዩዋቸውም።
የሚቀምሱት እህል ፣ የሚለብሱት ልብስ፣ ጋደም የሚሉበት ቦታም የላቸውም። በአንድ በአት ለሶስት አራት የሚያድሩበት በጣም አሳዛኝ ያለበት ነው።

እነዚህ መነኮሳት ታድያ የራሳቸውን ስጋዊ መከራ ችለው፤ ሌተቀን ስለ ሀገር ደህንነት ፣ ስለ አሀቲ ቤተክርስቲያን፣ ስለ ሰው ልጅ ሰላምና ጤንነት የሚፀልዩ ናቸው።

እነሱ በዚህ ከባድ ፈተና ውስጥ ሆነው ስለኛ እየደከሙ የሚገኙት ቢሆንም እኛ ግን እያየናቸው አይደለም ለዓለም ፈተና አጋልጠናቸዋል።

እነሱስ አለማዊ ህይወታቸውን በክርስትስ ፍቅር ወድቀው መከራውን ለመቀበል የተዘጋጁ ናቸው ፥ እኛ ግን ይህንን እያየን እንዴትስ ብሎ እንቅልፍ ሊወስደን ይችላል? በተሸለሙ ቤቶቻችን ዝም ብለን ለመቀመጥ ጊዜው አይደለምና እነዚህ ገዳማውያን ልንጎበኛቸው አለንላችሁ ልንላቸው ይገባል።

ከፀሎትና ከድካም መልስ የሚጠለሉበትን ፣ ከፆም መልስ የሚቀምሱትን ነገር ልናቀርብላቸው ይገባል። ለሰማያዊ ህይወታችን ስንቅ ይሆነናል ከመነኮሳቱ ፀሎት የበረከት ተካፋይ እንሆናለን፥ ለህሊናችንም እረፍት እናገኝበታለን።

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444

Leave a Comment