banner

በኤሌክትሪክ ቻርጅ የሚሰሩ እስከ 6 ሰው መጫን የሚችሉት ሳፊ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች

#FastMereja I ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ እየተለመዱ የመጡትና በኤሌክትሪክ ቻርጅ የሚሰሩ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ሳፊ (SAFI) የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ሲሆን በአንድ ጊዜ እስከ 6 ሰዎችን መጫን አቅም እንዳላቸውም በኦዳ ማኑፋክቸሪንግ የአማራ ክልል ሰሜን ሪጅን ተወካይ የሆኑት አቶ አሰፋ ለገሰ ለዘጋቢያችን ተናግረዋል።

ለነዳጁ ውድነት መፍትሔ የሆኑት ሳፊ ባጃጅ በቤት ውስጥ ለሞባይል ስልክ ፍጆታ በሚውለው የኤሌክትሪክ ኃይል ቻርጅ መደረግ እንደሚችሉም ገልጸዋል። እንዲሀም በባህር ዳር ፡ በጎንደር እና ሰመራ ላይ ወኪል መሆን የሚፈልግ በጋራ አብሮ መስራት አንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ሳፊ ባጃጅ የመለዋወጫ ዕቃዎች እጥረት እንዳይኖር በቂ መለዋወጫ ያቀረበ ሲሆን ለጥገናም ታስቦ በርካታ ወጣቶችን እንዳሰለጠኑም እንደሆነ አቶ አሰፋ የተናገሩት የአዲስ አበባ ቢሮ ሃያት አካባቢ መሆኑን ገልጿል።

የሳፊ ባጃጅ ዋና መገጣጠሚያውን በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ ያደረገው ኦዳ ማኑፋክቸሪንግ ሌሎች ተያያዥ ስራዎችንም የሚያከናውን ሲሆን በጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ መመረቁ ይታወቃል።
ዘጋቢ አለምነሽ ኩምሳ ከከቦልቻ




5 comments

Sara Bint Hbesha November 6, 2024 - 12:49 pm

Wagachew sent new yet new yemigeghut
Esti teru info setun

Reply
Chafi Selemon Thomas November 6, 2024 - 12:52 pm

ደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ ወክል ያስፈልጋል

Reply
Danuu Danuu November 6, 2024 - 12:52 pm

ከዛ ጩኸት ዳነ ህዝቡ በተለይ አዳማ!

Reply
Ware Jelesika November 6, 2024 - 12:52 pm

Waga sint new

Reply
Tekalign Shiferaw Shallo November 6, 2024 - 12:52 pm

እኛ ጋ ከገባ 3 ወር ቆይተዋል።

Reply

Leave a Comment