#FastMereja I ፊናፍ ፊልም በቴሌቲቪ መተግበሪያ ከዛሬ ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለህዝብ መታየት እንደሚጀምር ተገለፀ።
በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የተሰራው ፊናፍ ፈልም ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት በግል እና በመንግስት ሲኒማ ቤቶች ለተመልካች እይታ ቀርቦ ነበር። በወቅቱም ከተመልካች አዎንታዊ ምላሽ ማግኘት የቻለ ተወዳጅ ፊልም ነው ተብሏል::
በቢቂላ አስፋው ተጽፎ የተዘጋጀው ፊናፍ ፊልም አንጋፋ እና አዳዲስ ተዋንያኖች ተሳትፈውበታል። ፊናፍ የድራማ ዘውግ ያለው 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው ፈልም ሲሆን እንግሊዘኛ ሰብታይትል እንዳለው አቶ ቢቂላ አስፋው ገልጸዋል።
በጉማ፣ ኦዳ እና ለዛ አዋርዶች እጩ መሆን የቻለው ይህ ፊልም በ9ኛው የጉማ አዋርድ ላይም ተስፋ የተጣለበት ተዋናይ የውድድር ዘርፍ ብሩከ ግርማ ከፊናፍ ፊልም አሸናፊ መሆን ችሏል።
ቴሌቲቪን ፈልማቸውን ለማሳየት ተሰማሚ ምርጫ ሆኖ እንዳገኙት የተናገሩት አቶ ቢቂላ ብዙሃኑ ህብረተሰብ ጋር ለመድረስ ድንቅ አማራጭ መሆኑን ተናግረዋል። ቴሌቲቪ በቅርቡ የራስ መንገድ የተሰኘ ፊልምን ወደ መተግበሪያው ማስገባቱ የሚታወቅ ሲሆን ከርቤ የተሰኘ አዲስ ፊልምም አሁን ላይ በመተግበሪያው ላይ ይገኛል።
ከነዚህ ፊልሞች በተጨማሪም ዘጋቢ ፊልሞችንም በቴሌቲቪ መተግበሪያ ላይ ተመልካቾች በነጻ ማግኘት እንደሚችሉ የኢግል-ላይን መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በእርሱፈቃድ ጌታቸው ገልጸዋል።
ቴሌቲቪ በኢግልላይን ሲስተም ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያዉያን እዚሁ ሃገራችን ዉስጥ የበለጸገ ፕላትፎርም ነው። አሁን ላይ በቴሌቲቪ መተግበሪያ ፊናፍ ፊልምን ጨምሮ 8 የተመረጡ ሃገርኛ ፊልሞች ይገኙበታል።





8 comments
እ
ሚኒልክ ጡት ሲቆርት የሚያሳይ ይሆናል እንግድህ ሌላ ምን አለ kkkkkkkkk
በትግርኛ ፣ በጉራጊኛ ……. የሚሰራ ፊልምም እንዲሁ እንጠብቃለን ፡፡
Subtitle english yetgnaw americawi endiyayew nw wegegnoch
እኔ ሁሉንም ሰማለሁ ችግር የለብኝም ብቻ ክፈሉልኝ
በርቱ 😍
በትርጉም ይቅረብን
ጋላክሲ ፊልም ሰራ😂