banner

አክራሪ አሜሪካዊያን ሴቶች በወንዶች ላይ የወሲብ ማዕቀብ እንዲጣል ያለመ ዘመቻ ጀመሩ

ባሳለፍነው ማክሰኞ የተደረገው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጉዳይ አሁንም ዓለምን ትኩረት መሳቡን ቀጥሏል፡፡

የምርጫው ዋነኛ ተፎካካሪዎች የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሀሪስ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ጽንስ ማቋረጥ ጉዳይ ዋነኛ የክርክር አጀንዳ ነበር፡፡

የዲሞክራት ፓርቲ ዕጩዋ ካማላ ሀሪስ ጽንስ ማቋረጥ ጉዳይ የሰዎች መብት መሆን አለበት፣ ውሳኔው ለግለሰቦች መሰጠት አለበት በሚል ስትከራከር የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ ይህ የሰዎች መብት ቢሆንም በጉዳዩ ዙሪያ መወሰን ያለባቸው ግዛቶች ናቸው የሚል አቋም አላቸው፡፡

ሁለቱም እጩዎች በጉዳዩ ዙሪያ አቋማቸውን ግልጽ ማድረጋቸውን ተከትሎ ወንዶች እና የሀሳቡ ደጋፊ የሆኑ ሴቶች ድምጻቸውን ለዶናልድ ትራምፕ መስጠታቸውን ተከትሎ ምርጫውን አሸንፈዋል፡፡

የምርጫው ውጤት መታወቁን ተከትሎ የሴትነት አክራሪ አሜሪካዊያን ሴቶች መብታችን ተነፍጓል በሚል ሴቶች በወንዶች ላይ የወሲብ ማዕቀብ ሊጥሉ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ የተጀመረው ይህ ዘመቻ ወንዶች ነጻነታችን ነፍገው በአካላችን መደሰት አይችሉም ሲሉም ጥሪያቸውን እንዳስተላለፉ ዘ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡

ከተላለፉ መልዕክቶች በተጨማሪም ሴቶች ለፍቅር አጋር መፈለጊያ ተብለው የለሙ የመገናኛ መተግበሪያዎችን ከስልካቸው ላይ እንዲያጠፉ እና ክልከላውም ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት እንዲቆይ የሚሉም ይገኙበታል፡፡

ከአሜሪካ ባለፈም መሰረቱን በደቡብ ኮሪያ ያደረገው “4ቢ” የተሰኘው የሴትነት ንቅናቄ የዶናልድ ትራምፕን መመረጥ መቃወሙን እና ዘመቻውን እንደተቀላቀለ አስታውቋል፡፡

“4ቢ” የተሰኘው ይህ ንቅናቄ የኮሪያ ቋንቋ አራት ቃላት የተፈጠረ ሲሆን ትርጉሙም የፍቅር ቀጠሮ አንይዝም፣ ልጅ አንወልድም፣ ወሲብ አንፈጽምም፣ አናገባም የሚል ትርጉም ያለው ነው፡፡

ዘገባው የዐል ዐይም ነው።

10 comments

Arefayne Afiy November 8, 2024 - 9:04 am

ማን ተጎዳ ታዲያ 🤔

Reply
Na Home November 8, 2024 - 9:05 am

እዴ ደስታው የጋራችን መስሎኝ 😭😭😭

Reply
Esu Man November 8, 2024 - 9:06 am

የኛ ብቻ ነው ደስታው😂

Reply
Temesgen Gezahegn Bereded November 8, 2024 - 9:06 am

የኛም ሀገር ፌሚኒስቶች ጉዞ ወደ 4B ነው።

Reply
Kiru Bel November 8, 2024 - 9:06 am

😂😂😂 ይሄ ሁሉ ማንን ለመጉዳት ነው

Reply
Shame Abdi November 8, 2024 - 9:07 am

ለአራት ቀን የሚችሉ ይመስላቸዋል?

Reply
Esmiz Ro November 8, 2024 - 9:08 am

እና ጎብኚዎች ሊበዙብን ነው በለና😂😂

Reply
Dere Dawit November 8, 2024 - 9:10 am

ባሏን ጎዳሁ ብላ እንትንዋን ወጋች በጩቤ አሉ

Reply
Dink AB November 8, 2024 - 9:14 am

የኛ ሀገሮቹ ፌምኒስቶችም ጉዟቸዉ ወደ 4B ነዋ 🤔

Reply
Kiya Negn November 8, 2024 - 9:14 am

ዓለም መጥፍያዋን በገዛ እጇ እያፋጠነች ነው ።

Reply

Leave a Comment