banner

በአፍሪካ አህጉር ትልቁ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ተከፈተ

#FastMereja I ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ከ250 በላይ የፋሽን፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎችን በአንድ ጣራ ስር የሚያሰባስበው የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት ዛሬ ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተከፈተ።

ዝግጅቱ አለም አቀፍ ብራንዶችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና ፈጣሪዎችን በአንድ ጣሪያ ስር በማሰብሰብ እስካሁን ከተደረጉት ዝግጅቶች ትልቁ ያደርገዋል ተብሏል።

የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በጨርቃ ጨርቅ፣ በአልባሳት እና የቆዳ እሴት ሰንሰለቶች መካከል ትብብርን በማጎልበት እና ንግድን በማመቻቸት በአህጉሪቱ ትልቁ የፋሽን መድርክ ሆኖ ቆይቷል።

ዛሬ የተከፈተው እና ለመጪዎቹ አምስት ቀናት በሚቆየው የፋሽን፣ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎችን በአንድ ጣራ ስር የሚያሰባስበው ዝግጅት ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ከ250 በላይ የዘርፉ ተዋኒያኖች ኤግዚቢሽኖችን ያሳያሉ:: ከ60 በላይ ሀገራት የሚመጡ ከ7,000 በላይ የንግድ አቀለጣጣፊዎችም የታደማሉ ተብሏል። ይህም ለጎብኚዎች እና ተሳታፊዎች በፋሽን ኢንደስትሪ ዘርፍ አለም የደረሰችበትን ደረጃ አንዲገነዘቡ፣ ፈጠራዎች የት እንደደረሱ አጠቃላይ እይታ ይሰጣል ተብሏል።

ተሳታፊዎች እና ጎብኚዎች ወቅታዊን የጨርቃጨርቅ፣ ሌዘር እና ፋሽን ኢንዱስትሪ በተመለከተ በኮንፈረንሶች እና የፓናል ውይይቶች ላይ ለመሳተፍ እድል ያገኛሉ።

የዘርፉ በለሞያዎች በአፍሪካ የፋሽን እይታ ላይ በዘለቄታው መሰራት ስላለባቸው ጉዳዮች ፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና የኢንቨስትመንት መላዎች ላይ ያተኮሩ የፓናል ውይይቶች ያቀርባሉ።

በአፍሪካ አህጉር ትልቁ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን የሆነው 10ኛው የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ከዛሬ ጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።





1 comment

Kibrom Ashenafi November 8, 2024 - 12:15 pm

ኢትዮጵያ በኣሁኑ ሰኣት የሚያስፈልጋት ሰላም ብቻ ነው ።

Reply

Leave a Comment