0
#FastMereja I ተከሳሽ የኔው ብርሀኑ የእንጅባራ ከተማ አሰተዳደር ነዋሪ ሲሆን በጥቅምት 19/ 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ከቢዳ ጀጎላ ት/ቤት የሚማረውን የ14 ዓመት ወንድሙን ስልክ በመደወል የእናታችንን ልብስ ውሰድ ብሎ ከት/ቤት ከአሰወጣው በኋላ በማገት ከወላጅ ቤተሰቦቹ 1,000,000/አንድ ሚሊዮን ብር/ መጠየቁን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።
በሁኔታው የተደናገጡት የታጋች ቤተሰቦች ወዲያውኑ ለእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ በሰጡት ጥቆማ በተደረገ ብርቱ ክትትል በሶስተኛው ቀን ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ሲሆን ከተደበቀበት ቢዳጀጎላ ቀበሌ ልዩ ስፍራ አማያስቲ ጎጥ ላይ እጅ ከፍንጅ ተይዟል።
ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል የላከ ሲሆን መዝገቡ የቀረበለት የአዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ የኔው ብርሃኑ በ7 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል ሲል አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዋና ክፍል ያደረሰን መረጃ ያሳያል።

10 comments
ወዴት ወዴት
የጉድ ሀገር💔
ይሄ ሚሊዮን ግን የሰው ስም ነው ወይስ…?🙄
ሁለቱም እኮ ናቸዉ የታገቱት😥
ገና የማናየውና የማንሰማው ጉድ የለም
አይ ስምንተኛው ሽ (8 ኛው ሺ)
ይመቸው
ኧረ ፈጠራ 👌😀 ስልጣን ይሰጠዉ
እግዚኦ!!
ገና እናታቸውን አግተው ብር ይጠይቃሉ እድሜ ለብልፅግና ምን ያላየነው ያልሰማነው አለ😔