banner

ከ116 ዓመት ቦኋላ በtiktok የተቀረፈው ትልቁ የቤ/ክ ችግር

የነበሩት ችግሮች አመታትን ያስቆጠረውን ቤ/ክ ሙሉ ለሙሉ ሊያዘጉት ጥቂት ብቻ ነበር የቀራቸው የዚህ አንጋፋና ጥንታዊ የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን 116 ዓመት ያስቆጠረ
ሲሆን መገኛውም በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በደንዲ ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት የጋሬ ደብረ ሰላም አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ነው።

ከ 2 ዓመት በፊት የካህናት ልብሰ ተክህኖ የሌለው ቤተ ክርስትያኑ ዘመናትን በማስቆጠሩ እየፈራረሰ የሚገኝ የካህናት ደመዎዝ ለመክፈል ባለመቻሉ ሊዘጋ የነበር ሲሆን በወቅቱ በዲ/ን አቤኔዘር ውብሸት ብርቱ ጥረት ወደ ሚዲያ በtiktok page ከተለቀቀ በኋላ ይህ ጥንታዊና ታሪካዊ የአባታችን ቤተክርስቲያን 10 ሙሉ የካህናት መቀደሻ ልብስና የካህናት ደመዎዝ በወቅቱ የተሸፈነ ሲሆን

ቤተክርስቲያኑ ከጥንታዊነቱ በተጨማሪ በእድሜ ብዛት ውስጡ አዋራና የውጪ በረንዳ እየፈረሰ ስለነበር በአፋጣኝ እድሳት ሊደረግለት ስለሚገባ የካቲት 30 /2015 እድሳቱን በመጀመር ህዳር 1/2017 ዓ/ም የተመረቀ ሲሆን ይህ የአባታችን ጥንታዊ ቤተ ክርስትያን እስከ ተመረቀበት ቀን ድረስ ሙሉ ወጪው የተሸፈነው በዲ/ን አኔቤዘር የtiktok ቤተሰቦች የተሸፈነ ሲሆን ዘመናትን ያስቆጠሩ የቤተ ክርስትያኑ ችግሮች በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ተቀርፈዋል ።

በtiktok platform እንዲህም አይነት ቁም ነገር መስራት ይቻላል ።ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን ለሚገኙ ምእመናን መጪው ጊዜ ምን እንደሚመስል ከገለጠላቸው በኋላ አያይዞ እንዴት መኖር እንዳለባቸው መክሮአቸዋል፡፡ ስለመጪው ጊዜ ሲነግራቸው
‹‹ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና›› ብሏቸዋል፡፡

እንዴት መኖር እንዳለባቸው ሲመክራቸው ደግሞ ‹‹እንደ ጥበበኞች›› በጥበብ መመላለስ እንደሚገባቸው፤ ዳግመኛም ‹‹በጥንቃቄ›› እና ‹‹በመጠበቅ›› እየኖሩ ዘመኑን እንዲዋጁ አሳስቧቸዋል፡፡ (ኤፌ5.15-16)
ስለዚህም ዘመኑ ባመጣው social media ቤተ ክርስትያንን ካሉባት ችግር እያወጡ ዘመንን ዋጅቶ ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ለትውልድ ማሻገር ይቻላል።





Leave a Comment