#FastMereja I በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባምንጭ ከተማ የሚገነባውን ዓለም አቀፍ ስቴዲየም የገቢ ማሰባቢያ አስመልክቶ ዛሬ ሕዳር 03/2017 ዓ.ም በሐርመኒ ሆቴል መገለጫ ተሰጥቷል።
የአፍሪካ ዋንጫ እና የአለም አቀፍ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ማስተናገድ የሚችል እንደሆነ የተነገረለት ይህ ስቴዲየም 30ሺ ተመልካች የመያዝ አቅም እንዳለው ተገልጿል። እንዲሁም የመሮጫ ትራክ ስላለው የአትሌቲክስ ውድድሮችን ማስተናገድ ይችላል።
የካፍ ስታንዳርድ የሚያሟላ ካታጎሪ ሶስት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እስከ 30ሺ ተመልካች ማስተናገድ የሚችል ስቴዲየም መሆኑ ተገልጿል።
አጠቃላይ የስቴዲየሙ ግንባታ ወጪ 3 ቢሊዮን ብር ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ስራ 6 ወር እና ቀጣይ ሁለተኛ ዙር ምዕራፍ በ6 ወር በአጠቃላይ በአንድ አመት ለማጠናቀቅ ታቅዷል።
ዛሬ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው ከእሺ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት ተደርጓል። እሺ ሚዲያ ለዚህ ስታዲየም ግንባታ ቁልፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ እቅዶቹን ይፋ ያደረገ ሲሆን ዝግጅቱን በሀገር ውስጥ ሬዲዮ፣ ቲቪ ጣቢያዎች፣ ጋዜጦች በስፋት እንዲሰራጭ በማድረግ ማህበረሰቡን በማሳወቅ ይጀመራል ተብሏል።
ዲጂታል ዘመቻዎች፣ አምባሳደሮች ታዋቂ/ተፀእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በአምባሳደርነት በመሰየም ፕሮጀክቱን እንደያስተዋውቁ ማድረግ፣ በቀጥታ ስርጭት የሚከናወን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት፣ ስፖንሰርሺፕ፣ የሩጫ ውድድር፣ የእግር ኳስ ግጥሚያ፣ ኮንሰርት፣ ቶምቦላ ሎተሪ፣ በመዋጮና በልገሳዎች ገቢ ማሰባሰብ እንደታሰበ ተነግሯል።
በአሁኑ ወቅት የሲቪል ግንባታ አፈፃፀም 37% መድረሱ ተገልጿል።




10 comments
መልካም 😊!
ጭራሸ ህዝብ ነዉ የሚገነባዉ ቀልዳቹ እኮ በየቀኑ አይጣል ነዉ ለደሀ ቤት ገንቡ
Lemagn yemelata lj
ዓለም አቀፍ 👀 እረ ተዉ
እያንዳንዱ ኢትዮፒያዊ አንዳንድ ብር ብያዋጣ መገንባት ይቻላል አካውንት ከፈለጋቹ የኔን ውሰዱ
ምን አለበት ተጋግዛችሁ የተጀመሩት ሳያልቁ መፍረስ ሳይጀምሩ ብትጨርሷቸው ከዛ ደሞ በመተጋገዝ አዲስ ደሞ ትሰራላችሁ ደሞ እኮ ኳሱ ቢኖር ጥሩ ነበር
ሁሉም ልመና
ስታዴየሙን ስንዴ ዝሩበት ያኔ እናዋጣለን 🤗
Zim bilachu matechati min y miluti nw Ewikati masiloachu nwa yih auni maberatati nw inji comment metsafi gideta ayidalmi eko 😬😷
Rediet Kebede እያዋጣን 🙏