banner

#የጠየከውን አታገኝም?

ሰው መሆን በራሱ ወደ ላይ ማንጋጠጥ፣ አንዱ ጥያቄ ሲመለስ ሌላ መጠየቅ፣ አንዱ ፍላጎት ሲሟላ ሌላኛው ላይ ማተኮር ያለበት ነው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ እጅግ አጥብቀን ፈጣሪያችንን ጠይቀን የማናገኛቸው ነገሮች ያጋጥሙናል፡፡

ሌሎች በቀላሉ የሚያገኟቸው እኛ ግን ነጋ ጠባ ፈጣሪያችንን ወትውተን ያላገኘነው ነገር ይኖራል፡፡ አልፎ ተርፎም ይህ አጥብቀን የምንሻው ነገር ሊኖረን እንደሚገባ በበርካቶች ዘንድ የሚታመንበት፣ ጥቂት የማይባሉ ሰዎችም እርግጠኛ ሆነው እንዳለን የሚያስቡት ይሆናል፡፡

ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በረከቱ ይደርብንና እንዲህ ይለናል፡፡ “እግዚአብሔርን ደጋግመህ ጠይቀኸው ያልሰጠህ ነገር ካለ፣ አንተን ደጋግመው ጠይቀውህ ያልሰጠሃቸው ሰዎች እንዳሉ አስብ፡፡” እግዚአብሔር “ፈታሒ በጽድቅ ኮናኒ በርትዕ“ ነውና እንደየስራችን ይከፍለናል፡፡

እገዛችንን ልንሰጣቸው እየቻልን አልፈናቸው የሔድን ስንቶች ናቸው? ጩኸታቸውን እንዳንሰማ መስኮታችንን የዘጋንባቸው፣ ወይም ዳንኪራችንን ከፍ አድርገን ጩኸታቸውን የዋጥንባቸው ስንቶች ናቸው?

የትኛውን ጥሪ ነው በአጽንኦት የሰማነው? ስለበደላችን በቀራንዮ አደባባይ “ኤሎሔ… ኤሎሔ… ላማ ሰበቅታኒ” አባት ሆይ ለምን ተውኸኝ ያለው ጥሪ የኛ አይደለምን? እርሱ የሁሉ ባለቤት ሲሆን “ተጠማሁ” ማለቱ የኛን መጠማት ለማርካት ደሙን ሲያፈስ ያሰማው ነው፡፡ ሞቱ፣ ግርፋቱ… የኛን ሞትና ግርፋት የተቀበለበት ፍጹም ፍቅሩ የተገለጸበት ድንቅ ስጦታው ነው፡፡

ይህን ያህል ዋጋ ከከፈለልን ለጥቂቷ ዓለማዊ ጥያቄያችን ደጋግመን ጠይቀን ካልተሰጠን ወደ ራሳችን እንመልከት፡፡

በአስቸጋሪ ሁኔታ የበረሀው ሐሩር የሌት ቁር የሚፈራረቅባቸው፣ ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ ግርማ ሌሊቱን ድምጸ አራዊቱን ጸብአ አጋንንቱን ታግሰው፣ ዓለምን ንቀው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ በሚገኘውና ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ያሉበት ይኖራሉ፡፡

መነኮሳቱና ገዳማውያኑ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈታተኗቸው ነውና በአታቸውን ለማጽናት እጃችንን እንድንዘርጋ ደጋግመው ጥሪያቸውን ያቀርባሉ፡፡ እንስማቸው!!!

የሙትአንሳ የማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም የኛን እገዛ ከመቼውም ግዜ በላይ ይፈልጋል።

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444

Leave a Comment