banner

በቀብር ስፍራ በመገኘት የቲክቶክ ቪዲዮ ሲሰሩ የቆዩ ወጣቶች በፖሊስ ተያዙ

#FastMereja I በቀጨኔ ወረዳ 4 ቀጨኔ ዘላቂ ማረፊያ በሚባለው የቀብር ቦታ በመገኘት ሙዚቃ በመክፈት የቲክቶክ ቪዲዮ እየሰሩ ሲለቁ የነበሩ ወጣቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ወጣቶች መካከል አንዱ ድርጊቱን የፈፀምነው ተመልካችን ለማዝናናት ብለን ነበር ተጠያቂ እንደሚያደርግ ባለማወቃችን ስህተት ፈፅመናል ብሏል።

ድርጊታቸው በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 493 የሙታንን ሰላም እና ክብር መንካት በሚል እንደሚያስጠይቅ ከዚህ ቀደም መምህር፣ ጠበቃና የህግ አማካሪ አበባየሁ ጌታ መረጃን አካፍለን ነበር።




10 comments

Frita Alex November 17, 2024 - 9:30 am

በቁም አናታችን ላይ እየጨ ፈ ሩ ብ ን
ለሬሳ ማዘን በእውነት ሰብአዊነት ነው
አዲስ አበባ ፖሊስ እናመሰግናለን😻

Reply
Tesfaye Gemechu November 17, 2024 - 9:31 am

A law that care about a corpus than a living one, funny country 😂😂😂😂

Reply
Semu Arsenal Ethiopia November 17, 2024 - 9:32 am

እነዚህን ከሙታን መቀላቀል ነው

Reply
Ab Milko November 17, 2024 - 9:32 am

ለሙታን ሠላም☺️😏

Reply
Bereket Habtamu Mengistu November 17, 2024 - 9:33 am

ስንኖር የማንከበርባት ስንሞት የምንከበርባት ድንቅ ሀገር አለችን 😔🥴

Reply
Solomon Birhane November 17, 2024 - 9:33 am

የሙታን ሰላም፡መንካት

Reply
Fikadu Tesfaye November 17, 2024 - 9:33 am

ሌላው ጆን ዳንኤል

Reply
Tewodros Girma November 17, 2024 - 9:34 am

ሁሉም ሰው የቀበረው የቤተሰብ አባል አለው ፡ ሀውልት እያሳዩ ሲጨፍሩ ዝም ካልናቸው ነገ ደግሞ ቆፍረው አውጥተው የትሪለርን የዳንስ ሙቭ ሞክሩ ማለታቸው አይቀርም ፡ ደግሞም የሆነ ሰው ተበሳጭቶ ከሚጎዳቸው የተወሰነ ተምረው ታርመው መውጣታቸው መልካም ነው

Reply
Abebayehu Geta Enaro November 17, 2024 - 9:35 am

ይኼው ነው👌 #Fast_Mereja ዎች አመሠግናለሁ🙏

Reply
Melese Tefo Worasa November 17, 2024 - 9:35 am

ሰው ት/ቤት ሳይሄድ በአከባቢው የሆነ ሰው የሚያመስለውን ነገር መማር ያለበት ይመስለኛል።

Reply

Leave a Comment