banner

ችግሩ ተፈትዋል…???

ለ ዓመታት የቆየ መፍትሔ ማይገኝለት የመሰለ ችግር ባልተጠበቀ ጊዜ እና ባልታሰበ ሁኔታ መፍትሔ አግኝቷል ከ ሰሞኑን በ ዲ/ን አቤኔዘር ውብሸት በtiktok ቤተሰቦቹ አማካኝነት በጊንጪ ደንዲ ወረዳ የሚገኘው 116 ዐመት ያስቆጠረው የጋሬ ደብረ ሰላም አቡነ ተ/ሀይማኖት ቤ/ክ በአዲስ መልኩ ታድሶ ከተመረቀ የቅርብ ቀን ትውስታ ነው።

ለአመታት ከ 10 የማይበልጡ አባ ወራዎች በአካባቢያቸው ላይ ያለው ባዶ ቦታ ላይ መስቀል በመትከል በየወሩ በ24 በቦታው ላይ ተሰባስበው ተክልዬን ይዘክሩ ነበር ሰው ከሞተም ፍትሐት ሳይፈታ ባዶ ቦታውን እንደ ቤተ ክርስትያን በመጠቀም ይቀብሩ ነበር ይሄም ቤ/ክ ስለሌላቸው ቁጡራቸው በጣም ጥቂት በመሆን ይቸገሩ የነበሩ አባቶች እና እናቶች በብዕፁ አባታችን አቡነ ይስሐቅ በወላይታ ሶዶ ሀገረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ መልካም ፍቃድ እና ክትትል እንዲሁም በዲ/ን አቤኔዘር ውብሸት የtiktok ቤተሰቦች ሙሉ የግንባታ ወጪ በመሸፈን ለአመታት የተክልዬ ቤተ ክርስትያን ነው ብለው በባዶ መሬት ላይ ያለ ቤተ መቅደስ ፀሎት ሲያደርጉ የነበሩ 10 የሚሆኑ አባ ወራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የተክልዬ ቤ/ክ ተሰርቶ በዛሬው እለት በቀን 08/03/2017 ተመርቋል።

የዚህ ቦታ መገኛውም በወላይታ ሶዶ ሀገረ ስብከት በሁምቦ ወረዳ የኮይሻ ጎላ ኦቤያ አቡነ ተ/ሀይማኖት ቤ/ክ ነው ልብ በሉ ቤተ ክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤ ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡

ለዝያም ነው ለዘመናት ንፁህ ልብ ይዘው የፈጣሪ ቤት አንድ
ቀን እኛ ጋር ይመጣል ብለው በእምነት ሲፀልዩ የነበሩ 10 ብቻ የሚሆኑ አባ ወራዎች ዛሬ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው የቤ/ክ ባለቤት የሆኑት::





9 comments

Dabbaal Mootii November 17, 2024 - 8:53 am

ጊንጪ ደንዲ ወረዳ የምገኘው ምዕ/ሸዋ ዉስጥ የአምቦ ጎረቤትነው

Reply
ተስፍዬ በቀለ November 17, 2024 - 8:55 am

እግዚአብሔር ይመስገን ።

Reply
Weyinishet Wedajo November 17, 2024 - 8:55 am

ዲ/ን አቤነዘር ዉብሸት እግዚአብሔር ያገልግሎት ዘመንህን ይባርክ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ!!እኛንም የበረከት ሥራ ሰርተን እንድናልፍ ፈጣሪ ይርዳን🙏

Reply
Polijohnny Yohannes Solomon November 17, 2024 - 9:03 am

ተመስገን

Reply
Mihret Chubato Mahi November 17, 2024 - 9:06 am

እግዚአብሔር ይመስገን

Reply
Demissie Tafa November 17, 2024 - 9:06 am

ምንድነው የምለው? የጊንጪው ተክልዬ ቤ/ክ ነው ወይስ ስለ ወላይታ? ይህ ጊንጪ አይደለም! የተደበላለቀ ዜና

Reply
Abera Kogna Geda November 17, 2024 - 9:08 am

“ልጄ ሆይ ሰው ሁን” ይላል መጽሐፍ ቅዱስ።
ሰው ስትሆን እንደ ሰው ታስባለ።
ከሁሉም በላይ ፈጣሪ ይባርካችሁ!!!

Reply
Dnber Enkuhan November 17, 2024 - 9:09 am

እንኳን ደስ አለን አላችሁ

Reply
Ras Jah Mesaria November 17, 2024 - 9:09 am

🤣 mndnw mitachisut? Dendi bleh wolaita lay chereskewu eko😡…..

Reply

Leave a Comment