banner

ላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጵያ በአነስተኛ ቢዝነስ ላይ ለተሰማሩ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ድጋፍ አደረገ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ እና ሀዲያ ዞን በላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጵያ ግብረ ሰናይ ድርጅት አማካኝነት በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች የ 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደርጓል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተር ፕራይዝ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የከተማ ዘርፍ ሀላፊ ታምራት ተስፋሁን እንደገለጹት በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ከ350 ሺ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከዚህ ውስጥ 80 በመቶውን በቋሚነት የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል።

ላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጵያ ግብረ ሰናይ ድርጅት የመንግስትን ፕሮግራሞች ለመደገፍ የወጣቶችን እና ሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እያደረገ ያለውን ጥረት አብራርተዋል።

ወጣቶች ከትንሽ ሀብት ተነስተው ወደ ኢንቬስትመንት የሚሸጋገሩበትን እድል ለመፍጠር የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አመላክተዋል።

በተያዘው በጀት አመት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ባለፉት አራት ወራት ብቻ ከ46 ሺ በላይ ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ያሉት ምክትል ኃላፊው የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎችን በማመቻቸት ውጤታማ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ሲሉም ጠቁመዋል።

የላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጵያ ድርጅትስራ አስኪያጅ አቶ አክሊሉ ገ/ሚካኤል እንደገለጹት ተቋሙ በትምህርት፣በጤና እና የወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

እንደ ሀገር በወጣቶች እና ሴቶች የስራ እድል ተጠቃሚነት ላይ ያለውን መሰረታዊ ችግር ለመፍታት ከስልጠና በተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል።

ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር በተለይም ከጀርመን የኢኮኖሚ ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር በክልሉ በሀዲያ እና ስልጤ ዞን ወጣቶችን በማህበር በማደራጀት የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ላለፉት ሁለት አመታት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

የስራ እድል በመፍጠር እና ድህነትን በመዋጋት የሀገርን ኢኮኖሚ መገንባት ይቻላል ያሉት ስራ አስኪያጁ የተገለሉ እና በስራ እድል ፈጠራ ርቀው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ማጎልበት ላይ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም አቶ አክሊሉ አብራርተዋል።

በክልሉ በሀዲያ እና ስልጤ ዞኖች ከጀርመን የኢኮኖሚ ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር የወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማሳደግ የሚያስችል የአምስት አመት የልማት ፕሮግራም በመቅረጽ እየተሰራ መሆኑንም ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል።

የስራ እድልን በመፍጠር ድህነትን ማስቀረት ላይ መሰረት በማድረግ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

የወጣቶችን ንቃተ ህሊና በማዳበር ለተሻለ ለውጥ እንዲተጉ ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑ የተናገሩት አቶ አክሊሉ ከስልጠናና ትምህርት በተጨማሪ የብድር አቅርቦት በማመቻቸት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ላለፉት ሁለት አመታት በቢዝነስ እንቅስቃሴያቸው የተሻለ ተሳትፎ ያላቸውን 26 ማህበራትን በመመልመያ መስፈርት መሰረት በመለየት እና የስራ ፍላጎታቸውን መሰረት በማድረግ 3 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

የስልጤ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተር ፕራይዝ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱረህማን ወርቅቾ በዞኑ
የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ ላቭ ኢን አክሽን በዘርፉ ድጋፍ እያደረገ ያለውን ስራ አድንሸው የወጣቶችን የስራ እድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደ ሀገር ለተያዘው የዕድገትም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።





Leave a Comment