banner

በሱፍቃድ ሪል እስቴት ታዋቂዋን ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ

በ5 ቢሊዮን ብር እየተገነባ ያለው በሱፍቃድ ሪል እስቴት አዳጊ የሆነችውን አረርቲ ከተማ ከአዳማ፣ ደብረዘይት፣ ሞጆ፣ ደብረብርሃን እና አዲስ አበባ ጋር በልማት፣ የቱሪስት መዳረሻ እና በኮንፍረንስ ቱሪዝም የማስተሳሰር ዐቅም እየፈጠረ የሚገኘው የቤት ልማት ኢንቨስትመንት ብራንዱን ይበልጥ ለማሳደግና በቀጣይ ዓለም-አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋት ይረዳ ዘንድ ዛሬ ቅዳሜ ሕዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ2 ዓመታት ብራንድ አምባሳደር አድርጎ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ እና ዝነኛዋን ጋዜጠኛ እጸገነት ይልማን የኩባንያው ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙን በዛሬው ዕለት አስታውቋል።

በሱፍቃድ ሪል እስቴት ልማት ኩባንያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምንጃር ሸንኮራዋ አረርቲ ከተማ ስትጠራ ስሙ አብሮ የሚነሳው በሱፍቃድ ሪል ስቴት በ230,000 ካሬ ሜትር ላይ እየተገነባ ያለው ግዙፍ የመኖሪያ መንደር 1,000 ቤቶችን፣ ባለ 5 ኮኮብ ሆቴል፣ ከአጸደ-ሕጻናት እስከ ኮሌጅ ድረስ ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት ተቋም እና የጤና ተቋማት፣ ለስምጥ ሸለቆዋ የቱሪስት መዳረሻ አረርቲ ተስማሚ የመዝናኛ ስፍራዎችን ያካተተ አዲስ መንደር ነው።

ከተመሰረተ ገና የሁለት ዓመታት ዕድሜ ያለውና በአማራ ክልል በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ እየተገነባ ያለው በሱፍቃድ ሪል እስቴት የቤት ፈላጊዎችን ምርጫ ያሟላና ዘመናዊ መንደር እየፈጠረ ይገኛል። ከዋና ዋና ከተሞች ወጣ ብሎ ወረዳዎችንና አዳጊ ከተሞችን በማነቃቃት፣ የኢንዱስትሪ ልማት ፍሰቶቻቸውን የሚያግዝ፣ የማኅበረሰቡን አኗኗር በማዘመን የከተማ ልማት እያፋጠኑ ከሚገኙ ጥቂት ፕሮጀክቶች ቀዳሚ እንደሆነ ይነገርለታል።

ይህ በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ እየተገነባ ያለው አዲስ የመኖሪያ መንደር ለቤት ደንበኞቹ አስተማማኝ የቤት ግንባታ አገልግሎት እና የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ በማድረግ አሳታፊ የከተማ ልማት ፍልስፍና ይከተላል ተብሏል።

በሱፍቃድ ሪል እስቴት በአጭር ጊዜ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የቤት ደንበኞችን ያፈራ ሲሆን፤ ከሰሜን አሜሪካና ካናዳ፣ እስራኤል፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ኡጋንዳ እና ቻይና አገራት የሚኖሩ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ በስፋት የቤት ደነበኞቹ የሚገኙባቸው አገራት ናቸው። ይህ አለም-አቀፍ ተደራሽነቱን እያሰፋ በመሄድ ሌሎች አገራትንም የመድረስ ስትራቴጂ ነድፎ እየሰራ ሲሆን የዛሬው የብራንድ አምባሳደር ሹመትም የዚሁ አካል ነው ተብሏል።





1 comment

kalkidan November 23, 2024 - 2:04 pm

Good luck,, i wish you good work time.

Reply

Leave a Comment