ከጥራት ጋር ቤተሰብ ሆነው ጥሪት ያፍሩ የሚለው ጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ የምስረታ ሂደቱን አጠናቆ በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ መጀመሩን አሳውቋል።
ጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ በይፍ የቁጠባ ፣ የብድር፤ የፈንድ ማስተዳደርና የንግድ ስራ ማማከር ከጀመረበት ጥቅምት 05 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ 204 አዳድስ የቁጠባ አካውንቶችን በተሳካ ሁኔታ በማስከፈት ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የቁጠባ ገንዘብ ከደንበኞች ማግኘት የቻለ ሲሆን ለአራት ተበዳሪ ደንበኞች 900 ሽህ ብር ብድር መስጠቱንም ገልጿል ::
ጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ በኢፌዴሪ አዋጅ ቁጥር 626/2001′ አዋጅ ቁጥር 1164/2012 እና በአድሱ የንግድ ህግ መሠረት በ82 ባለ ራዕይ የአክሲዮን ባለቤቶች ተመስርቷል፡፡
በ25.7 ሚሊዮን ብር በተከፈለ ካፒታል የተመሠረተው ጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ የፍይናንስ ተቋም ዘርፍ ለሀገር እና ህብረተሰብ የኢኮኖሚ እድገት መፋጠን ያለውን ሚና በተረዱ መስራች ባለአክሲዮኖች ውጣውረዶችን አልፈው ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በኢ.ብ.ባ የአነስተኛ የፍይናንስ ስራ ፍቃድ ቁጥር 068/2024 አግኝቶ ስረውን ጀምሯል፡፡
ጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ ለህብረተስቡ የቁጠባ፤ የፈንድ አስተዳድርና የንግድ ስራ ማማከር አገልግሎቶችን ለመስጠት ቀልጣፋ የብድር! የመጀመሪያውን ዐብይ ቅርንጫፍ ሳፋር ቅርንጫፍ ብሎ በመሰየም 4E ህንፃ 2ኛ ወለል ላይ ከፍቷል።
በቅርቡም ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ እና በሸገር ክፍለ ከተማ አስተዳድር በኮዬ ቅርንጫፎቹም በቅርቡ ስራ እንደሚጀመር አሳውቋል።
በተጨማሪም ከአላሚ ኢንደስትሪያል ኢንጅነሪንግ እህት ኩባንያ ከሆነው አላሚ ፋጣን የመልዕክት አገልግሎት ጋር በአጋርነት ለመስራት የተስማማ ሲሆን ሴቶች የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ገዝተው ወደ ስራ እንዲገቡ 30 በመቶ በጥሪት ማይክሮ ፋይናንስ በመቆጠብ በተመቻቸው ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተገልጿል፡፡




