የቴሌቲቪ ቲክቶክ ቻሌንጅ አሸናፊዎች የ አይፎን 15 series ስልክ ተሸለሙ። ከፍተኛ እይታ እና ላይክ በማግኘትከ 1-3 የወጡት የቴሌቲቪ ቲክቶክ ቻሌንጅ አሸናፊዎች በዛሬው ዕለት ተሸልመዋል። ከሃምሌ 26 / 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 / 2016 ዓ.ም ድረስ በቲክቶክ ማህበራዊ ገጽ ላይ በቆየው የቴሌቲቪ ቻሌንጅ ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ እይታ እና ላይክ ያገኙት አሸናፊዎች በዛሬው ዕለት ከኤግልላይን መስራች እና ዋ/አስኪያጅ በርሱፍቃድ ጌታቸው ሽልማት ተቀብለዋል።
መስከረም 30 በተሰበሰበው መረጃ መሰረት
👉 1ኛ የወጣችው 3.4 ሚሊዮን እይታ እና 145.7k ላይክ በማግኘት ነፃነት ታምራት ወይንም በቲክቶክ ስሟ (netsu_tam)፤
👉የ2ኛ ደረጃን የያዘው 2.1 ሚሊዮን እይታ እና 137.1K ላይክ በማግኘት ያገኘው ያቤጽ በላይ ወይንም (yab_ets) እና
👉3ተኛ ደርጃ መውጣት ተሸላሚ የሆነው ዳዊት ፀጋዬ በቲክቶክ ስሙ (daolic ) 2.1 ሚሊዮን እይታ እና 90.2K ላይክ በማግኘት አሸናፊ ሆነዋል።
በቀጣይ ብዙ ተመልካቾችን አሸናፊ ማድረግ የሚችል እጣ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን አቶ በርሱፊቃድ ጌታቸው ለተዳሚዎች ገልጸዋል።
Eaglelion system Technology ሰኔ 27 2016 ዓ.ም በኢትዮ ቴሌኮም አጋርነት ቴሌቲቪን ይፋ ሲደረግ ትዝታ እና 6 ሰአት ከለሊቱ ፊልሞች ይዞ ነበር ።በአህኑ ወቅት ሁለቱ ፊልሞችን ጨምሮ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያገኙ 8 ሃገርኛ ፊልሞች በመተበሪያው ላይ ይገኛሉ ።እነሱም “ዶቃ”፣” ጥቁር አደይ”፣” ቁራኛዬ” ፣ ” የራስ መንገድ” ፣ ” ከርቤ” እና “ፊናፍ” ናቸው።
አንድ ሰው በቴሌቲቪ መተግበሪያ ፊልሞችን ለመለከት በቅድሚያ የቴሌቲቪቭን መተግበሪያ ማውረድ እና መመዝገብ ይጠበቅበታል። በተጨማሪም ቴሌቲቪ ለሃገር ዉስጥ ክፍያ ከቴሌብር ዲጂታል የክፍያ ሶሉሽን ጋር የተሳሰረ ሲሆን ከሀገር ዉጪ ለሚገኙ ተመልካቾች ደግሞ የአለም አቀፍ የክፍያ ካርድ ማለትም visa card a, master card እና American express card በመጠቀም ክፍያ መፈጸም ይችላል።




